አዝ፦ ሰዶም ገሞራ (4x) ሰው እግዚአብሔርን አይፈራ ሰዶም ገሞራ ግርግር ነው ከተማው አንዱ ሌላውን አይሰማው ሁሉም ይሮጣል ለንግዱ ጐዳናው ጠቧል መንገዱ ለነፍሱ አያስብ ለሰማይ ቤቱ ለዛሬ ብቻ ለለት ለለቱ አዝ፦ ሰዶም ገሞራ (4x) ሰው እግዚአብሔርን አይፈራ ሰዶም ገሞራ ወንድ ከወንድ ጋብቻ ሴትም ከሴት ጋር ጋብቻ በፍትወት እሳት ሲቃጠል ሲጋደም በየስርቻ እንሰሳ ሆነ አዬ! ክቡር ሰው መድኋኒት የለሽ ደዌ ጨረሰው አዝ፦ ሰዶም ገሞራ (4x) ሰው እግዚአብሔርን አይፈራ ሰዶም ገሞራ ሕጻን አይሉ አዋቂ አንዱ በሌላው ሸማቂ ቀድሞ ጣዩ አልታወቀ እንጂ ሰው ሁሉ ጨብጧል ፈንጂ የፍቅር ኑሮ የዕርቅ ሰላም ክፋት ጠረገው ጠፋ ካለም አዝ፦ ሰዶም ገሞራ (4x) ሰው እግዚአብሔርን አይፈራ ሰዶም ገሞራ ልጅ የናቱን ሆድ ረገጠ አባት ልጁን ገላመጠ እናትም ጣለች ልጇን ቀረቀረችው ደጇን ጣራው ዘበጠ ቤቱ ተናጋ ዳኛ ጠፋና የሚያረጋጋ አዝ፦ ሰዶም ገሞራ (4x) ሰው እግዚአብሔርን አይፈራ ሰዶም ገሞራ