Song Lyrics

ጌታ ሆይ አትመጣም ሆይ

Pastor Tamrat Haile
Ahunim Alew Bemerkebu
በእሳት ቁጥቋጦ የተገለጥከው የአብርሃም የይስሐቅ የያዕቆብ አምላክ ነኝ ያልከው መርዛሙን እባብ በትር ያደረክ በምስኪን ነገር ባሕሩን የከፈልክ መርዙን አውጣልን ከበትራችን መድሃኒት አርገን ለምድራችን አዝ፦ ጌታ ሆይ የሱስ ሆይ ጌታ ሆይ አትመጣም ሆይ ጽድቅን ያደረግን እየመሰለን ባዶ ቅንአት እያቃጠለን የሕሊናን ድምጽ ተግሳጽን ንቆ እግራችን ሲሮጥ ወደ ደማስቆ በጽድቅ ጸሐይ ተገለጠልን የአይናችንን ቅርፊት ጣልልን አዝ፦ ጌታ ሆይ የሱስ ሆይ ጌታ ሆይ አትመጣም ሆይ ፍቅራችን ያንገት የለበጣ ነው ከአንተ አይደለም ከየት አመጣነው አንዱን ከሌላው እንለያለን ልብን አይደለም ልብስ እናያለን ልባችን ጨካኝ ለሰው አይራራ ዳስልንና ዓይናችን ይብራ አዝ፦ ጌታ ሆይ የሱስ ሆይ ጌታ ሆይ አትመጣም ሆይ የዕምነት አባቶች የቀደሙቱ ለፍቅር ኖረው ለፍቅር ሞቱ ታሪክ አንባቢ ሆነን ቀርተናል ከአንተ በስተቀር ማን ይችለናል የነሱ አምላክ ዛሬም ሕያው ነህ እባክህ ጐብኘን ለስምህ ብለህ አዝ፦ ጌታ ሆይ የሱስ ሆይ ጌታ ሆይ አትመጣም ሆይ እሳትህ ቢነድ እንነጥራለን መዶሻ ብትልክ እንሰባበራለን ውኃ ብታፈስ እንጸዳለን ዝም ካልከን ግን እንጐዳለን ዛሬም ወዳንተ መጥተናልና ቤትህን ሙላ በክብር ዳመና አዝ፦ ጌታ ሆይ የሱስ ሆይ ጌታ ሆይ አትመጣም ሆይ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection