Song Lyrics

ስሙኝ እንጂ

Meheret Etefa
Leyet Yale New
ስለ አንተ በጆሮዬ ከሰማሁት ይልቅ (2x) በዓይኔ ያየሁት ለእኔ ሆነብኝ ድንቅ (2x) የእኔ ጌታ ተባረክ የእኔ ጌታ (4x) እግዚአብሔር ለምን እንዲህ አረክ አይባልም (2x) የሚሰራውን ያውቃል ፍፁም አይዘነጋም (2x) የእኔ ጌታ ተባረክ የእኔ ጌታ (4x) ምሥጋናዬ (4x) ይድረስ ለአንተ ብቻ ጌታዬ (2x) እግዚአብሔር ህዝቡን መታደግን ያውቃል (2x) ካስፈለገ ደግሞ ፀሐይን ያቆማል (2x) የእኔ ጌታ ተባረክ የእኔ ጌታ (4x) እግዚአብሔር አምላኬ ጌታ ነው ዓለም ሁሉ በሙሉ የእርሱ ነው (2x) የእኔ ጌታ ተባረክ የእኔ ጌታ (4x) እግዚአብሔር አምላክን አትጠራጠሩት ያደርጋል ብላችሁ በእውነት እመኑት ስሙኝ እንጂ (2x) እግዚአብሔር አምላክን አትጠራጠሩት ያደርጋል ብላችሁ በእውነት እመኑት ስሙኝ እንጂ (2x) እስቲ ላስታውሳችሁ ትውስ አለኝ እኔም አምላኬ የሰራው ከዚህ ቀደም ስሙኝ እንጂ (2x) የኤርትራን ባሕር ኧረ ማን ከፈለው ውኃውን እንደ ግድግዳ ኧረ ማን አቆመው ስሙኝ እንጂ (2x) የመንፈስ የመንፈስ የመንፈሱን እንጂ የሥጋውን መስማት ያስጥላል ከደጅ ስሙኝ እንጂ (2x) በምድረ በዳ ላይ ይህን ያደርጋል ከቶ ለምን አልከው አይቻለውም ወይ ስሙኝ እንጂ (2x) ምሥጋናዬ (4x) ይድረስ ለአንተ ብቻ ጌታዬ (2x) አቤት ውበቱ የተዓምራቱ ለጠበቀው ሰው እስከ ሰዓቱ ሊመጣ ሲልም አረፋፈዱ ሊነጋ ሲልም መጨላለሙ አርፍዶ ይነሳል ሁሉን ይቀድማል የተዓምራቱን ውበት ያሳያል (2x) አቤት ውበቱ የተዓምራቱ ለጠበቀው ሰው እስከ ሰዓቱ ሊመጣ ሲልም አረፋፈዱ ሊነጋ ሲልም መጨላለሙ አርፍዶ ይነሳል ሁሉን ይቀድማል የተዓምራቱን ውበት ያሳያል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection