ጊዜው እጅግ ከባድና አሰቃቂ ጊዜ ነበር ኦሆ ከሰውነቱ የሚወጣው ላብ እና ደም ነጠብጣብ ነበር ኦሆ የጐልጐታው ታሪክማ ስንቱ ይወራ ስንቱ ይነግር ኦሆ ልረሳው ልዘነጋው እኔ አልችልም ይህንን ነገር እስቲ ላክብርህ እስቲ ላንግስ ወድሃልሁ ጌታ ያለልክ (2x) የረሃቡ የጥማቱ የመብረዱ የመንቀጥቀጡ አቤት ጭንቅት አቤት ስቃይ ይህ ሁሉ እኮ ለእኔ ነዉ እነሆ ክብር እነሆ አምልኮ እነሆ ስግደት ይገባሃል እኮ (2x) ይገርማል ሥራህ ይገርማል ችሎታህ ይገርማል ፍቅርህ ይገርማል ማዳንህ ኦሆ ይገርማል ፍቅርህ (2x) ያንን የሚያህል ትልቅ መስቀል ተሸክሞ ተራራውን ወጥቶ ተጨነቀ ተሰቃየ እንዲህ እንዲያ ተገባው እስቲ ላክብርህ እስቲ ልንበርከክ ወድሃልሁ ጌታ ያለልክ (2x) ይገርማል ሥራህ ይገርማል ችሎታህ ይገርማል ፍቅርህ ይገርማል ማዳንህ ኦሆ ይገርማል ፍቅርህ (3x)