Song Lyrics

ፍቅርህ ነክቶኛል

Meheret Etefa
Leyet Yale New
ምህረትህና ቸርነትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል እለት እለት ክቡር ደሙ ይሸፍነኛል ይጠብቀኛል ሃሌሉያ ቤትህ ያገቡኛል ታማኙ እጅህ መቼ ይጥላል ታማኙ እጅህ ቤት ያደርሳል (2x) ሃሌሉያ ቤትህ ያገቡኛል ዝም ዝም አትበል ነፍሴ ትለኛለች የአምላኳን ውለታ ሁሌም ታስባለች (2x) እንዴት የምን ዝም ዝም ዝምታ በልቤ ለሞላው ጌታ ፍቅርህ ነክቶኛል ልመስክርልህ ሰው ሁሉ ይወቅ ማያውቅ አለ እንዴ ሃሌሉያ እኔ አንተን ልውደድ ሁልጊዜ አመልክሃለሁ (2x) ሃሌሉያ በጣም እወድሃለሁ ሁልጊዜ አመልክሃለሁ (2x) ሃሌሉያ በጣም እወድሃለሁ እንዴት የምን ዝም ዝም ዝምታ በልቤ ለሞላው ጌታ ፍቅርህ ነክቶኛል ልመስክርልህ ሰው ሁሉ ይወቅ ማያውቅ አለ እንዴ ሃሌሉያ እኔ አንተን ልውደድ ያለፈው ዘመኔ አለፈ አለፈ ዳግመኛ ላላየው ያለፈው ኑሮዬ አለፈ አለፈ ዳግመኛ ላላየው ቀሪውን ዘመኔን ባርከው ባርከው የአንተው ለአንተው አድርገው ያለአንተ መኖር ከቶ አይሆንልኝም ከእንግዲህ እንካ ተቆጣጠረኝ ከእንግዲህ እንካ እንካ ጌታ ተቆጣጠረኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection