Song Lyrics

እስቲ ላነሳሳው

Meheret Etefa
Leyet Yale New
የእርሱን ጥበብ ታላቅነት ምስክር ነው የሰራው ፍጥረት (2x) ሁሉም ያውራ ይተርክለት ቃሉን ሥራውን ይጨዋወቱት (2x) እኔስ ላውራለት ቅኔን ልቀኝለት ቅኔን ልቀኝለት (2x) እስቲ ላነሳሳው (3x) እስቲ ልናገረው የጌታዬ ሥራው በሙሉ ድንቅ ነው ሥሙን እየጠራሁ እስቲ ልወድሰው አያልቅበት እርሱ ብቻውን ጌታ ነው (2x) የምድር ዕፅዋት የምድር እንስሳት ለቅጽበት አይቆሙም ያለ አንተ ምህረት (2x) የአቀማመጥቸው አቤት የውበታቸው ቢታቱ ቢታዩ የማይጠገቡ ናቸው (2x) አምልኮው ለአንተ ዝማሬው ለአንተ ዕልልታው ለአንተ ጭብጨባው ለአንተ (2x) እስቲ ላነሳሳው (3x) እስቲ ልናገረው የጌታዬ ሥራው በሙሉ ድንቅ ነው ሥሙን እየጠራሁ እስቲ ልወድሰው አያልቅበት እርሱ ብቻውን ጌታ ነው (2x) ሁሉን የሚችለው የአምላክ እስትንፋስ ፈጠረኝ አበጃጀኝና ሕይወትንም ሰጠኝ (2x) የፈጠርከኝ ጌታ እኔም አከብርሃለው ስለ አንተ ላወራ ይኸው መጥቻለሁ (2x) አምልኮው ለአንተ ዝማሬው ለአንተ ዕልልታው ለአንተ ጭብጨባው ለአንተ (2x) እስቲ ላነሳሳው (3x) እስቲ ልናገረው የጌታዬ ሥራው በሙሉ ድንቅ ነው ሥሙን እየጠራሁ እስቲ ልወድሰው አያልቅበት እርሱ ብቻውን ጌታ ነው (2x) አምልኮው ለአንተ ዝማሬው ለአንተ ዕልልታው ለአንተ ጭብጨባው ለአንተ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection