Song Lyrics

ለየት ያለ ነው

Meheret Etefa
Leyet Yale New
አላሳልፈኝ ያለው የብረት መዝጊያው ኧረ እንዴት ተከፈተ አሁን በጊዜው (2x) ባለስልጣኑን ጌታ በእኔ ሲያየው ለመከፈት መነካት አላስፈለገው (2x) አልፈራም ነገን ምን እሆን ብዬ እኖራለሁ በእርሱ ተደላድዬ አልሰጋም ነገን ምን እሆን ብዬ እኖራለሁ በእርሱ ተደላድዬ ኧረ ምን ችግር አለ ጌታዬ እግዚአብሔር አለ (2x) ኧረ ምን ችግር አለ እርሱ እግዚአብሔር አያለ ኧረ ምን ችግር አለ ጌታዬ እግዚአብሔር አለ እሄዳለሁኝ ገና አላቋርጥም በእኔ ያለው እርሱ ፍፁም አይደክምም (2x) በኃይልና በብርታት በእኔ ሳይሆን በመንፈሱ በእግዚአብሔር ችላለሁ ሁሉን (2x) በእርሱ ታምኜ ምን እሆናለሁ በትከሻው መሃል ላይ በክብር አድራለሁ (2x) ኧረ ምን ችግር አለ ጌታዬ እግዚአብሔር አለ (2x) ኧረ ምን ችግር አለ እርሱ እግዚአብሔር አያለ ኧረ ምን ችግር አለ ጌታዬ እግዚአብሔር አለ እስቲ ልናገር ስለዚህ ጌታ አሃ የጠላቴን ትጥቅ አቤት ሲያስፈታ (3x) አደራረጉ ከሰው ልዩ ነው ኦሆ የእኔ እኮ ጌታ ለየት ያለ ነው ለየት ያለ ነው (2x) ቀን በቀን እኔ ማየው ቀን በቀን የሚያሳየኝ ጉድ እኮ ነው ቀን በቀን ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ በልጧል የማዳን እጁ ለእኔ ቀርቧል (2x) ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ በልጧል የማዳን እጁ ለእኔ ቀርቧል (2x) በተዐምር እወጣለሁ በተዐምር እገባለሁ የታመንኩበት ጌታዬ ተዐምረኛ ነው (2x) አሁን አሁንማ ብሷል አሁን አሁን (2x) እኔም አምነዋለሁ እርሱም ይሰራል ከተዐምራቱ እኔን ያጠግበኛል (2x) እኔም አምነዋለሁ እርሱም ይሰራል ከተዐምራቱ እኔን ያጠግበኛል (2x) እስቲ ልናገር ስለዚህ ጌታ አሃ የጠላቴን ትጥቅ አቤት ሲያስፈታ (3x) አደራረጉ ከሰው ልዩ ነው ኦሆ የእኔ እኮ ጌታ ለየት ያለ ነው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection