ቅዱስ ቅዱስ በክብር ያለኸው ዙፋንህ ከጥንት እስከ ዘላለም ነው ክብር ሞገስ ሁልግዜም አብሮህ ነው ሃሌ ሃሌሉያ እኔ አመልክሃለሁ 1. ቅዱስ እግዚያብሔር ቅዱስ እያሉህ ኪሩቤል ሱራፌል እንደሚያመልኩህ መላዕክት በአንድነት እንደሚሰግዱልህ እኔም አመልክሃለሁ ይኸው በፊትህ 2. የምድርን ውኾች በ እፍኝህ ሰፍረሃል የአለምን ተራሮች በሃይልህ አጽንተሃል ሽማግሌዎች ወድቀው ፊትህ ይሰግዱልሃል አቤቱ አምላክ ሆይ ማንስ ይመስልሃል 3. ቅዱስ ቅዱስ ብለው ሲዘመሩልህ ጳውሎስና ሲላስ ከልብ ሲያመልኩህ የወህኒውን መሰረት አናወጠው ሃይልህ በአምልኮ ውስጥ መጣ ታላቁ ክብርህ 4. አእወፍ ለእኛ ባይገባን ድምጻቸው ከትንሽ ጀምሮ ሁሉም በየቋንቋው ክበር ይሉሃል ያመሰግኑሃል እውነት ነው ጌታ ሆይ ክብር ይገባሃል