አዝ፦ በሰማይና በምድር በውስጡ ያለውን ነገር አስበህ ይሰራሃቸው አንተ ነህ እኮ እግዚአብሔር እጅጉን በጣም ይገርማል ጥበብህ ጌታ ያስደንቃል አቤት ዕውቀትህ ስራህ ሊወራልውህ/ሊነገርልህ ይገባህ (2x) አቤት (4x) ስለ ስጦታህ ምሕረትህ ተመስገን ስለ ጥበቃህ ስጦታህ ደስ ያሰኛል ልብን ይማርካል አንተን የሚመስል ኧረ ከየት ይገኛል (2x) አቤት (4x) ስለ ስጦታህ ምሕረትህ ተመስገን ስለ ጥበቃህ የምንተነፍሰው ሳንከፍልበት ዋጋ ሰጥተኸን እያየን ነውና የአንተን ፀጋ (2x) አቤት (4x) ስለ ስጦታህ ምሕረትህ ተመስገን ስለ ጥበቃህ ዓለማትን በቃልህ ፈጠርህ አፀናህ ለሰው ልጅ መልካም ነገር አበጀህ (2x) አቤት (4x) ስለ ስጦታህ ምሕረትህ ተመስገን ስለ ጥበቃህ የተራራ የወንዙ የባሕር የውቂያኖስ ፈጣሪ አንተ እኮ ነህ ለዘለዓለም ንገሥ (2x)