አዝ፦ ባለግርማ ባለግርማ ምሥጋናዬና አምልኮዬ ማደሪያህ ይግባ (2x) ባለሞገስ ባለሞገስ ምሥጋናዬና አምልኮዬ ማደሪያህ ይድረስ (2x) ከአንተ በቀር አምላክ እኔ አላመልክም ሌላ ሌላውን ልቤ አልፈቀደም እሺ አላለኝም (2x) ባለግርማ ባለግርማ ምሥጋናዬና አምልኮዬ ማደሪያህ ይግባ (2x) እንደ ሲድራቅ ሚሳቅ አብደናጐል ሰባት እጥፍ እሳቱ ቢነድም ለቆመው ምስል አልዘምር አላደርገውም ሰባት እጥፍ ይንደድ ምን ቸገረኝ የማመልከው ይችላል ሊያድነኝ በፈቃዴ ገባለሁ ይልቀቁኝ አያቃጥለኝም በዳንኤል እንደ እግዚአብሔር ሰው በአንበሶች ጉድጓድ እንደ ተጣለው [2] ግዑዙን አምላክ አላመልክም አላደርገውም ይራቡ አንበሶቹ ምን ቸገረኝ የማመልከው ካለልኝ ልሂድ ልግባ ይልቀቁኝ አይችሉም ሊበሉኝ ለእርሱ ክብር አፌን እከፍታለሁ ደስ እያለኝ እዘምርለታለሁ ጐንበስ ቀና እያልኩኝ ለእርሱ እሰግድለታለሁ እርሱ እኮ ነው በሕይወት ያኖረኝ መከራዬን በሙሉ ያስረሳኝ አልሰለችም እወድሰዋለሁ አመልከዋለሁ