አዝ፦ ቅኔን እቀኛለሁ ቅኔን እቀኛለሁ የእጆቹን ሥራ እያየሁ ትርጉም አለው ለእኔ አወራለሁ የማየውን አሃሃሃ በፊቱ ለማየት እጅግ ናፍቄ አንጐራጉራለሁ አንጐራጉራለሁ (2x) የፈጠራቸውን ፍጥረቶች እያየሁ ጌታን ከልብ ሆኜ አመሰግናለሁ (2x) አቤት ድንቅ አምላክ ነው ሥራው አይቆጠር እዘምራለሁኝ ለጌታዬ ክብር (2x) አዝ፦ ቅኔን እቀኛለሁ ቅኔን እቀኛለሁ የእጆቹን ሥራ እያየሁ ትርጉም አለው ለእኔ አወራለሁ የማየውን አሃሃሃ በፊቱ ለማየት እጅግ ናፍቄ አንጐራጉራለሁ አንጐራጉራለሁ ውበትን አገኙ ሰማያት በመንፈስህ የዓለምን ተራሮች በቃልህ አጸናህ (2x) እኔም ስለነርሱ ክብርን እሰጥሃልሁ የፍጥረት ፈጣሪ ተባርክ ብያለሁ (2x) አዝ፦ ቅኔን እቀኛለሁ ቅኔን እቀኛለሁ የእጆቹን ሥራ እያየሁ ትርጉም አለው ለእኔ አወራለሁ የማየውን አሃሃሃ በፊቱ ለማየት እጅግ ናፍቄ አንጐራጉራለሁ አንጐራጉራለሁ የሚታየውንም ማይታየውንም በላይ በሠማይ ቢሆን በታች በምድርም (2x) ሁሉን በየስፍራው አስተካክሎ አኖረው አቤት አቤት ሥራው እግዚአብሔር ጌታ ነው (2x) አዝ፦ ቅኔን እቀኛለሁ ቅኔን እቀኛለሁ የእጆቹን ሥራ እያየሁ ትርጉም አለው ለእኔ አወራለሁ የማየውን አሃሃሃ በፊቱ ለማየት እጅግ ናፍቄ አንጐራጉራለሁ አንጐራጉራለሁ (2x)