ከሚያስፈራው ከድቅድቁ ጨለማ ወደሚደነቅ የብርሃን ከተማ ሄደናል ተዘዋውረናል በዚያ የለንም ዳግም ከዚያ ከሞት ሰፈር አንገኝም ከምስራቅ ከምዕራብ ከደቡብ ከሰሜን በብርሃኑ ብርሃን እያየን ከነገድ ከዘር ቋንቋ ተዋጅተን በአንድነት ለኢየሱስ እንዘምራልን አባባት እያልን የምንኖርበት የልጅነትን ስልጣን ሰጥቶናል የብርሃን ዘር ምርጥ ዜጋ በኢየሱስ በኢየሱስ አግኝተናል አዝ፦ ኢየሩሳሌም (2x) እንገባለን ዘላልም በዚያ ዘለዓለም እንዘምራለን ሃሌሉያ ሃሌ ሃሌ (3x) ኢየሱስ ሃሌሉያ ኢየሱስ ሃሌሉያ ሃሌ ሃሌ (3x) ኢየሱስ ሃሌሉያ ኢየሱስ ማራናታ