1-ከተከሸኑ እልፍ ቃላት ከተመረጠ የቅኔ ብዛት ሀገሩን ከሞላው ዜማ የኔ ሕይወት ላንተ ይሰማ/ይሰዋ 2-ቢዘምርልህ ይህ አንደበቴ መልክህ በራቀው የእለት እለት ህይወቴ መስዋዕቴ ላንተ እኮ ነው የሌለህበት ላንተ ምንህ ነው መስዋዕቴ ላንተ እኮ ነው ያልከበርክበት ሁሉ ድካም ነው ይዘምር የእልፍኝ ሕይወቴ አምልኮዬ ይቅደም በቤቴ ልሁነው የዘመርኩትን በቃላት ያሰፈርኩትን ያምልክህ የጓዳ ህይወቴ ይዘምር ይቅደም በቤቴ ልሁነው የዘመርኩትን በዜማ ያመለኩትን ላምልክህ በህይወቴ በህይወቴ ይገዛ መላው እኔነቴ ላምልክህ በህይወቴ ላምልክህ በህይወቴ በህይወቴ ያምልክህ መላ'ው ሰውነቴ ላምልክህ በህይወቴ ላንተ መስዋዕት ይህ አይደል ወይ ያንተ ምስጋና ህይወት አይደል ወይ ያምልክህ መላው እኔነቴ ላምልክህ በሕይወቴ ላንተ መስዋዕት ንፁህ አይደል ወይ ያንተ ምስጋና ህይወት አይደል ወይ ያምልክህ መላው ሰውነቴ ላምልክህ በሕይወቴ