የተገባህ ምስጋና አንተ ነህ የኔ ጌታ የተገባ ክብር ላንተ ነው የኔ ጌታ በምስጋና ወደፊትህ እቀርባለሁ ላመልክህ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ይገባሀልና ለስምህ 1-በምስጋና የተፈራህ ገናና አምላክ ነህ ልዑል አምላክ ብንዘምርህ ብንሰግድልህ አይበቃህ እልፍ እእላፋት ያንተ ፍጥረት ላንተ ክብር ያዜማሉ ቀን ከለሊት ያንተን ስራ በምስጋና ያውጃሉ በማለዳ ምስጋናዬን አበዛለሁ እኔ አበዛለሁ በቀትርም ዝማሬዬን አበዛለሁ እኔ አበዛለሁ 2 ስምህ ሀያል የአማልክቱም አምላክ ገዢ ነህ ታላቅ ጌታ የሆነልህ ሰማይ ምድሩ ምስጋናህ መላዕክቱ ላንተ ሞገስ ላንተ ግርማ ይዘምራሉ ባይገልፅህም በአዲስ ቅኔ ምስጋናህን ያውዳሉ በማለዳ እኔ ብዙ ተደርጎልኛል ለኔ ብዙ ሆኖልኛል ከማመስገን በቀር ምን ይሻለኛል ከማመስገን በቀር ምን ይገልፅኛል እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን