Song Lyrics

አመልክሀለሁ

Amelkihalehu

አስቤ አስቤ አስቤ ያረክልኝን ከልቤ አመልክሀለሁ ክብሬ ነህ የከበርኩብህ ስሜ አስቤ አስቤ አስቤ የሆንክልኝን ቆጥሬ አመልክሀለሁ ሀይሌ ነህ የከበርኩብህ ስሜ 1-የለኝም አቅምና ጉልበት-ራሴን የማሳይበት የለኝም ከእግዚአብሔር ሌላ-አላውቅም ፈረስም ሰረገላ አንድ ነው የኔ ጉልበት-ደፍሬ ምሰብክለት/ምሰግድለት እግዚአብሔር ነው መመኪያዬ-አለኝ የምለው ጌታዬ አመልክሀለሁ አመልክሀለሁ አመልክሀለሁ አመልክሀለሁ 2-ከበዛው ፍቅርህ በስተቀር-ምን አለኝ ብልስ ልናገር አልቻልኩም የለኝምና-ያለኝን ይኸው ምስጋና ከማዳን ድንቅህ ጀምረህ-ያቆምከኝ እንዲህ አክብረህ ያክብርህ ዘሬ በሙሉ-ያምልኩህ አለህ ይበሉ አመልክሀለሁ አመልክሀለሁ አመልክሀለሁ አመልክሀለሁ ይህ አለኝ ይላል የኖረው-ይህ አለኝ ይላል የሞላው አለኝ ይላል ዶሴውን መዞ-ይህ አለኝ ይላል ያለውን ቆጥሮ ሰው አለኝ ይላል የኖረውን-ይህ አለኝ ይላል የሞላውን አለኝ ይላል ዶሴውን መዞ-ይህ አለኝ ይላል ያለውን ቆጥሮ እኔስ የለኝም ዶሴ አለኝ የምለው በራሴ እኔ አሳየለሁ ክብሬን የሞላኝን እኔ አሳያለሁ ሀብቴን/ኃይሌን የእግዚአብሔሩን ጉልበቴ ሆይ አቅሜ ነህ የኔ እግዚአብሔር ጋሻዬ ነህ እንዳንተ የረዳኝ ማነው እንዳንተ ያከበረኝ ማነው ብቃቴ ሆይ ሞገሴ ሆ የኔ ክብር መዕረጌ ሆይ ለኔ እንዳንተ ማነው ለኔ እንዳንተ ማነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection