Song Lyrics

ቸር

Cher

ቸርነትህ ብዙ ነው አያልቅም ባወራው ቸርነትህ ብዙ ነው ኧረ አያልቅም ባወራው እንደኔ ፍቅርህን ያዩ በምህረትህ ውለው ያደሩ ክበር ይሉሀል አንተን በዘመናት ያልተውከንን ቸርነትህን ያዩ በምህረትህ ውለው ያደሩ ክበር ይሉሀል አንተን ለዘመናት ያልጣልከንን ቸር ነህና ምህረትህ ለዘላለም ለዘላለም እንዳንተ ያለ የለም ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ለዘላለም እንደእግዚአብሔር የለም ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ለዘላለም እንደእግዚአብሔር የለም 1,ለፃድቁም ለኀጥኡ ፀሀይን አወጣህ ላልተገባን ሁሉ ምህረትን አበዛህ የሰው ልጅ በሙሉ ያንተ ጥገኛ ነው ይነጋል ይመሻል ይህ ደግነትህ ነው አመስግኑት ስገዱለት ክብር ስጡ ለእርሱ ምህረት እግዚአብሔር ደግ አባት ነው የፈጠረውን የማይተወው ክብር ስጡ አመስግኑ ዘምሩለት እልል በሉ እግዚአብሔር ደግ አባት ነው የፈጠረውን የሚያኖረው ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ለዘላለም እንደእግዚአብሔር የለም ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ለዘላለም እንደእግዚአብሔር የለም ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ለዘላለም እንደእግዚአብሔር የለም 2,በቸርነት በምህረቱ ያልተረዳ የለም በጎነቱ ብዙ እንደሰው አይደለም በመልካምነቱ ስንቱን ተሻገርን የማይገፋውን በድል እያለፍን አመስግኑት ስገዱለት ክብር ስጡ ለእርሱ ምህረት እግዚአብሔር ደግ አባት ነው የፈጠረውን የማይተወው ክብር ስጡ አመስግኑ ዘምሩለት እልል በሉ እግዚአብሔር ደግ አባት ነው የፈጠረውን የሚያኖረው ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ለዘላለም እንደእግዚአብሔር የለም ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ለዘላለም እንደእግዚአብሔር የለም ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም ለዘላለም እንደእግዚአብሔር የለም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection