Song Lyrics

ቅዱስ

Kidus

1-ያለህና የነበርህ በክብር የምትመጣ ለዘላለም የምትኖር የሰማይ የምድር ጌታ ምድር ከክብርህ ተሞልታለች ያንተን ክብር እያየች እኛም ባሪያዎችህ በፊትህ እንሰግዳለን ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እንዳንተ የለም ጌታ በኃይል የበረታ እንዳንተ የለም ጌታ በክብር የበረታ 2-የፅድቅ ነው ክብረዙፋንህ-ሁሉን ቻይ ግርማዊነትህ የገዢዎች ገዢ ነህ ሀያል-ሽረት የማይደርስብህ ሰማይ ሰራዊት ይመልኩሀል-ልዑል ግርማህ ያስፈራል ትልቁን ሀይል ይዘህ ነግሰህ-ማን ችሎ ፊትህ ይቆማል ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እንዳንተ የለም ጌታ በኃይል የበረታ እንዳንተ የለም ጌታ በክብር የበረታ በሰማይ በምድር የለም አንተን የሚመስል የዘመንህን ቁጥር የለም ከቶ የሚገድብ ምድር ከክብርህ ተሞልታለች ታላቅነትህን ታውጃለች ምድር ከክብርህ ተሞልታለች አምላክነትህን ታውጃለች በሰማይ በምድር የለም አንተን የሚመስልህ አልፋ ነህ ኦሜጋ አንተ ለብቻህ ምድር ከክብርህ ተሞልታለች ታላቅነትህን ታውጃለች ምድር ከክብርህ ተሞልታለች አምላክነትህን ታውጃለች እንዳንተ ያለ የለም በሰማይ እንዳንተ ያለ የለም ምድር ላይ ከምድርም በታች የለም አይኖርም ለዘላለም!
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection