ልቤ ብዙ ብዙ ይመኛል የአንተን ጥሎ ወዲያ ይሮጣል አሳልፈህ አትስጠኝ ለራሴ በአንተ ልኑር አልሁን በራሴ ልቤ ብዙ ብዙ ይመኛል የአንተን ጥሎ በራሱ ይሮጣል አሳልፈህ አትስጠኝ ለራሴ ደርሶ አሳቢ ስሆን ለራሴ እንደ ልብህ ልሁን እንደልብህ እንደ ሀሳብህ ልሁን እንደፈቃድህ (2x) ፈቃድህ በልቤ ላይ ትሁን ትሰረኝ በራሴም አልሁን ቀድመኸኝ ከወጣህ ከፊቴ አልፈራም ብርቱ ነኝ አባቴ ጥላህ ስር በምቾት አድራለሁ ዘመኔን በአንተ ስር ከአደረከው (2x) የተከፈተ በር ሁሉ ከአንተ አይደለም ነግ ሊያጐድለኝ እንጂ ለመልካም አይደለም ተደባሎቆ የገባን ስኬቴን አውጣልኝ ከቤቴ ከቤቴ ሁሉ የሞላበት የሃሰት ገነት ምን ሊበጅ ያለአንተ አንተ የለህበት ይሻል የለ የአንተው በረሃ ሳላይ እህል ውኃ (2x) ዝጋብኝ የስኬቴን መንገድ ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ የነገን እዳ እፈራለሁ ሰግቼ ለምን እኖራለሁ ይቅርብኝ የምቾቴን መንገድ ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ የነገን ቁጣ እፈራለሁ ሰግቼ ለምን እኖራለሁ እንደ ልብህ ልሁን እንደልብህ እንደ ሀሳብህ ልሁን እንደፈቃድህ (2x) የአንተን ውድ ጊዜ መጠበቅ አቅቶኝ የልብህን ሃሳብ መታገስ ተስኖኝ የፈጠንኩ ሲመስለኝ ዘግይቼ እንዳልገኝ ከአየኸው ወርጄ የእንጀራ ጩኸቴ ጽኑ ልመናዬ በሞላልኝ ማግስት እንዳይሆን ገዳዬ አንተ ያልከው ይሁን በሕይወቴ እኔ አልቅደም ቅደመኝ አባቴ ዝጋብኝ የስኬቴን መንገድ ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ የነገን እዳ እፈራለሁ ሰግቼ ለምን እኖራለሁ ይቅርብኝ የምቾቴን መንገድ ካልሆነ ካልመጣ ከአንተ ዘንድ የነገን ቁጣ እፈራለሁ ሰግቼ ለምን እኖራለሁ (2x) እንደ ልብህ ልሁን እንደልብህ እንደ ሀሳብህ ልሁን እንደፈቃድህ (2x)