ማን ያመልጣል ከእግዚአብሔር ማን ይሸሸጋል ከጌታ ቢገለጥ ታሪካችን ጉድ ነው የእኛ ገበና በአደባባይ ጨዋ ያረገን በግል መክሮ ያሳፈረን ዳኝነቱ ያልተገባን እኔን ጨምሮ ቤቱ ይቁጠረን ነግ በእኔ ማለት ጥሩ በተያዙበት መያዝ ሳይያዙ ጌታን እንደው እርሱ ይምራል ይህንንም ይቅር ይላል (2x) ምህረት የናቀ ዛሬም ይፈርዳል በተማረው ልክ ማን ሰው ይምራል (2x) እንከን የለሽ ኑሮ የለኝም ታሪኬ ቢመረመር ሌላው ላይ ስፍረድ ቆሜ ወድቆ እስኪሰበር የእርሱን ገሃድ የእኔ በቤቴ ፍርድ ገምድሎ የማንነቴ ብዙ የተማረ ብዙ ይምራል ነበር ትምህርቱ ማን ግድ ይለዋል? አምላክ አድርጐለት ሃጥያቱን ታሪክ ሰው አልምር ብሎት ሆነ የዕድሜ ልክ አትፍረጅ አትፍረጅ ተይ ነፍሴ ይፈረድብሻል አንቺ ተይ ምላሴ እያየሽ እየኖርሽ የእርሱን ምህረት እንዴት ግድ አይልሸም የሰው ሕይወት የማያልፈው . (1) . የእራሱን ቁስለት አያቆም መፍረድ በሰውም ማንነት ለከፋ ቁስል እንጨት ይሰዳል ለታመመ ሰው ይህ መች ይረዳል ኧረ ያዘኝ ያለህ ይላል ጪኸቱ አላሳልፍ ቢለው የሰው አንደበቱ በሰው አፍ ተመቶ እያነከሰ ስንቱ ተሰብሮ ከማይሆን ዋለ አሃሃ ማን ያመልጣል ከእግዚአብሔር ማን ይሸሸጋል ከጌታ ቢገለጥ ታሪካችን ጉድ ነው የእኛ ገበና በአደባባይ ጨዋ ያረገን በግል መክሮ ያሳፈረን ዳኝነቱ ያልተገባን እኔን ጨምሮ ቤቱ ይቁጠረን ነግ በእኔ ማለት ጥሩ በተያዙበት መያዝ ሳይያዙ ጌታን እንደው እርሱ ይምራል ይህንንም ይቅር ይላል (2x) ምህረት የናቀ ዛሬም ይፈርዳል በተማረው ልክ ማን ሰው ይምራል (2x)