Song Lyrics

ወቅት እንዳታበላሽ /ሀና ተክሌ

Hana Tekle
Yezelalem Fetari
ክረምት አልጠብቅም ክረምት ላይ ሆኜ በጋን እኔ አልሻም በጋ ላይ ቁጭ ብዬ እሰራለሁ አሁን ስራዬን አለቅም ዘመኔ ላይ ቆሜ ዘመን አልጠብቅም ጊዜዬ ነው ወቅቴ ነው ዘመኑ ነው ተራዬ እሰራለሁ እሮጣለሁ በወቅቱ ዘርቼ ከእርሱ እጠብቃለሁ ይረዳኛል አምናለሁ የተሰጠኝ ጊዜዬ ነው እሰራለሁ እሮጣለሁ በወቅቱ ዘርቼ ከእርሱ እጠብቃለሁ በጊዜ (4x) ትናንት ላልሆነለት ዛሬን አትንፈገው ከንፈርህን መጠህ ሁድህን አታስብሰው ተስፋ ለቆረጠው ምክር ካስፈለገ ዐይኑን ግለጥና አድርሰው ለነገ ትናንት ዛሬ አይደለም ዛሬ ሌላ ቀን ነው በትላንቱ ዛሬ ዛሬን ያረሰ ማነው የመጠውለግ ጸባይ አይሆንም ወዳጄ ወቅት እንዳታበላሽ ልንገርህ ማልጄ በጊዜ (4x) አሁን የዋልንበት ነው ለነገ ተስፋ የዘራነው ዘር ነው ሚጠብቀን ኋላ ከሰራነው ዛሬን ከተጋን በበርቱ እንደርሳለን ካልነው አይቀርም መድረሱ በጊዜ (4x) ክረምት አልጠብቅም ክረምት ላይ ሆኜ በጋን እኔ አልሻም በጋ ላይ ቁጭ ብዬ እሰራለሁ አሁን ስራዬን አለቅም ዘመኔ ላይ ቆሜ ዘመን አልጠብቅም ጊዜዬ ነው ወቅቴ ነው ዘመኑ ነው ተራዬ እሰራለሁ እሮጣለሁ በወቅቱ ዘርቼ ከእርሱ እጠብቃለሁ ይረዳኛል አምናለሁ የተሰጠኝ ጊዜዬ ነው እሰራለሁ እሮጣለሁ በወቅቱ ዘርቼ ከእርሱ እጠብቃለሁ በጊዜ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection