Song Lyrics

ያለ ምክንያት

Hana Tekle
Yezelalem Fetari
ስፈራ ስቸር ማልተነፍሰው ሚስጥሬ በዝቷል እኔ ባልናገር የልብ ወዳጄ የውስጤን ያውቃል እርሱ እንደሚያውቀኝ ሰው አያውቀኝም እንጂ መቆም አልችልም እንኳን በንጉሥ በራሴም ደጅ የምህረት ዓይኑ ዛሬም ያየኛል አልሰለቸኝም ይፈልገኛል (2x) ፈላጊዬ መሃሪዬ ኢየሱስ ወዳጄ አይዞሽ የሚለኝ እኔን ሚያበረታኝ ነው የልብ ወአጄ ነው ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ እንዳትወደኝ በመልካምነቴ ይህ አይደለም ማንነቴ እንዳትጠላኝ ደግሞ በጥፋቴ ፍቅር ነህ አያስችልህም አባቴ ያለ ምክንያት ወደህ በምክንያት አትጠላም ለምህረትህ ስፍር መለኪያ የለውም የአንተ ፍቅር መነሺያው ከራስህ የመውደድ ልብ የማያልቅብህ (2x) የእኔ ጌታ ከወዳጅ ከፍቶ ልጅህ ድርሻዬን ብሎ እርም እንዳላለ አልመች ቢለው የሸፈተበት አባቴን አለ አባትነቱን የበደል ብዛት መች ይሽረዋል ሁልን እረስቶ ደግሞ እንደገና ልጄ ይለዋል በምህረት ዓይኑ ዛሬም ያየኛል አልሰለቸኝም ይፈልገኛል የምህረት ዓይኑ ዛሬም ያየኛል አልሰለቸኝም ይፈልገኛል ፈላጊዬ መሃሪዬ ኢየሱስ ወዳጄ አይዞሽ የሚለኝ እኔን ሚያበረታኝ ነው የልብ ወአጄ ነው ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection