የምፈልገውን ሁሉ ባገኝ የምፈልገው ደስታ ጋራ አልደርስም ስደርስበት ይቀልብኛል ሳልጠግበው ይሰለቸኛል የእኔ ክፍተት ሌላ ነው ብርም ወርቅም አይደለም ኢየሱስ ነው ረሃቤ መንፈስ ነው ጥጋቤ በህልውናህ ሥር መሆን በአንተ መኖር ውሎ ማደር በመገኘትህ የታሰበ ሰዉ ምነኛ የታደለ ነው አስበኝ የእኔንም በህልውናህ በሚያጽናናው በመንፈስህ ይህ ነው ጥማቴ ይህ ነው ጉጉቴ ክብርህን ማየት ነው መሻቴ ትርቱም ለጠፋው ሕይወቴ ምላሽ ሲታጣ ከሞላው ቤቴ ለሞኖር ስዝል ሲደክመኝ ባዶነቴ ሲጮህብኝ የእኔ ክፍተት ሌላ ነው ያለኝ ነገር አይደለም ኢየሱስ ነህ ረሃቤ መንፈስው ነው ጥጋቤ በህልውናህ ሥር መሆን በአንተ መኖር ውሎ ማደር በመገኘትህ የታሰበ ሰዉ ምነኛ የታደለ ነው አስበኝ የእኔንም በህልውናህ በሚያጽናናው በመንፈስህ ይህ ነው ጥማቴ ይህ ነው ጉጉቴ ክብርህን ማየት ነው መሻቴ ህልሜ አንተን ማየት በኑሮዬ ህልሜ አንተን ማየት ነው ጉጉቴ የደስታዬ ልክ ሰላሜ እርካታዬ ጥግ ፍስሃዬ ኢየሱስ ይህ ነው ጥማቴ ይህ ነው ጉጉቴ ክብርህን ማየት ነው መሻቴ (2x)