Song Lyrics

ቤተ ሰሪ

Hana Tekle
Yezelalem Fetari
ባማረ ባጌጠ ቤት ውስጥ ተሰይሚያለሁ በተዋበ ህዝብ ተከብቢያለሁ ዙሪያዬን የማየው ሁሉ ለዓይን ይስባል እኔ ግን ታምሜ ውበቴ ጠፍቶኛል ከቤትህ ውስጥ እያለሁ እኔ ጐድያለሁ ለሚያየኝ ለስሞ እኔ እንዳለሁ አለሁ ቤትህን ሲሞላው ዕልልታና ሆታ እኔን የሚያውከኝ የነፍሴ ጭንቀቷ የአንተ ቤት እኔ ነኝ የእኔ ቤት ሌላ ነው ቤተ ሰሪው በዝቶ መላ የሚለኝ ማነው ቀርበህ ሳለህ ከደጅ ልትመጣ ወዳጄ እንዴት ይሆን የማይህ እሩቅ አገር ሄጄ ያዳራሹ ውበት እኔን ሸፍኖኛል ግዑዝ ከእኔ በልጦ አልፎ ይኮንነኛል በጌጥ የታጀበ ቤቱ ተሰርቶ አልቆ ልብ ሁሉ በእጁ ነው የእኔን ቦታ ወስዶ ይበል እርሱም ይመር ቦታም አይጥበበን ግን ለታደሰ ቤት ምነው አጉል አጉል ሆነ እኔ ካልተደስኩኝ ካልሆንኩኝ እንደ ቤቱ ትርጉም የለሽ ኑሮ ድካም ነው ለከንቱ ቃሉ ቀርቧል እያልን ፍጻሜ የዘመን ከንቱ ቤት ስንሰራ ዘለዓለሙን ትተን ተላልፈን እንናገር አቤቱ አደራ የተጣልን እንዳንሆን እንደነበር ሥምህን ስንተጠራ ሥምህን ስንተጠራ ሥምህን አደራ የነበርን ሥምህን ስንተጠራ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection