ሰውማ የእራሱ ችግር በዝቶበት ያዋየዋል ለጠናበት ለእራሱ መሆን አቅቶት ጭንቀት ሰፎት ማን ሊረዳው ማን አቤት ብሎት ውይ ሰው አልኩኝ እኔም በችግሬ ሁሉም ሲሰወር ከሰፈሬ አለሁ ያለኝ በደና ቀን ውሉ ጠፋብኝ በከፋኝ ቀን ዞር ስል ከሰዉም ከእራሴ ጌታ ነው ለካ መልሴ በይ ፀሎቴ (2x) ዛሬ አገናኘኝ ቶሎ ከአባቴ ላለቅስ ተደፍቼ እግሩ ሥር ወድቄ ስነሳ ፊቴ ብርቶ ልቤ በእርሱ ረክቶ ቢመለስም ባይመለሰም ጥያቄው ውስጤ ሰላለም ነው ከእኔ በላይ የሚያስብልኝ እርሱ አዋቂ ነው ብቻ አልሰወር አልጥፋ እንጂ እኔ ከሥሩ እንኳን ነገሬን እኔ አልፈዋለሁ ሙሉ ዘመኑን (በፀሎት) መልስ ይመለሳል በፀሎት ልብ ይጠበቃል በፀሎት በፀሎት በመንበርከክ (2x) ቅርብ ነው አጠገቤ ነው ጌታዬ የእኔ የሚለኝ ወዳጄ ታዲያ ለማን ለምን ብዬ እጨነቃለሁ ልመናዬን አስታውቃለሁ አእምሮን የሚያልፍ የአምላክ ሰላም ልቤን ሃሳቤን ይጠብቃል ደስ ይለኛል በእርሱ ሁልጊዜ ላይቀር ያለልኝ ባለው ጊዜ ሲገባኝ እውነቱ ለእራሴ ጌታ ነው ለካ መልሴ በይ ፀሎቴ (2x) ዛሬ አገናኘኝ ቶሎ ከአባቴ ባለቅስ ተደፍቼ እግሩ ሥር ወድቄ ስነሳ ፊቴ ብርቶ ልቤ በእርሱ ረክቶ ቢመለስም ባይመለሰም ጥያቄው ውስጤ ሰላለም ነው ከእኔ በላይ የሚያስብልኝ እርሱ አዋቂ ነው ብቻ አልሰወር አልጥፋ እንጂ እኔ ከሥሩ እንኳን ነገሬን እኔ አልፈዋለሁ ሙሉ ዘመኑን (በፀሎት) መልስ ይመለሳል በፀሎት ልብ ይጠበቃል በፀሎት በፀሎት በመንበርከክ (2x)