አላስተያይህም ከሚሆነው ከሁኔታው ጋራ ከሚመጣው ዳግም ከሚሄደው ከንፋስ ሽውታ ምክኒያቱ አንተ ነህ አንተን የማመልክበት በቂ ነው መዳኔ ከበቂም በላይ ነው መትረፌ ኢህን በሥልጣኑ ማድረግ ማን ቻለበት አይደለም ዎይ ያወጣኸኝ ከባርነት አይደለም ዎይ የፈታኸኝ ከእስራት ታዲያ እንዴት ነው መኖሩ ዳግም ተለይቶ ወጥቶ ከነጻነት ድሮዬን አልሻም ድሮዬን አልደግምም እኔ አልመለስም እስር ቤት አዝ፦ እኔ አልመለስም እስር ቤት አልመለስም እስር ቤት (3x) ውሻ ወደ ጥፋቱ እንዲመልስ አልገኝም ኋላዬን ስከልስ የያዝኩት መንገድ ገብቶኛል ልክ ነው ማን ያስተኛል ሕይወት ነው እውነት የሞላበት የሰላም ነው ቤቱ ያለንበት እጠራለሁ እንጂ ሌላውን ያልገባውን ያላየዉን እኔ አልመለስም እስር ቤት አዝ፦ አልመለስም እስር ቤት (2x) እኔ አልመለስም እስር ቤት (2x) አልመለስም እስር ቤት (2x) እኔ አልመለስም እስር ቤት (2x) ዴማስን ሳልሆን ጠላላ መንገድ ላይ ሳልቀር ከኋላ ከመቅበዝበዝ ሕይወት ድኛለሁ ከዓለም ፍቅር ተርፊያለሁ ዘምራለው ከቶ አልዘፍንም ጾሜ ታች አልወርድም እላይ ተሰይሜ አበራለሁ ገና መዳኔን ብርቁን ታሪክ የኢየሱሴን እኔ አልመለስም እስር ቤት አዝ፦ አልመለስም እስር ቤት (2x) እኔ አልመለስም እስር ቤት (2x) እኔ አልመለስም እስር ቤት (2x) አልመለስም እስር ቤት (2x)