Song Lyrics

ሰላም ነው

Hana Tekle
Yezelalem Fetari
መኖሪያዬ የዘለዓለም አምላክ የአባቶቼ የነ ሙሴ ኣባት እንደ እግዚኣብሔር ያለ ማንም የለም የሚያውቅልኝ እንደ አንተ አላገኝም ብታድነኝም ባታዳነኝም አንተ መልካም ነህ ይህንን አድርግ ያንን አታድርግ መች ትባላለህ ላደረራግህ ማስተካከያ ከማንም ኣትሻም ፍፁም በስራህ ፍፁም በምክርህ አትሳሳትም ያስጨነቀኝ ቀንበሬን ውስጤን አንቆ የያዘው ለእኔ አጅግ ቢከብደኝ ኢየሱሴ ለአንተ እንዴት እንዴት ቀላል ነው የዛሬው ድቅድቅ ሌሊቴ ይገባሃል ሚስጥሩ ፊትህን አያየሁ ዛሬ ግን አላለሁ ሰላም ነው አዝ፦ ሰላም ነው እላለሁ በእጅህ የገባውን ነገሬን እያየሁ ሰላም ነው እላለሁ ውስጤ ሸክም አዝሎ እጅህን አያየሁ አልገባሽ ቢለኝ ነገሩ ማዕበሉን ወጀቡን ፈርቼ ውስጤ ብርዱ ተሰማኝ ሰው ነኝና ሰግቼ ጉልበቴ እልሃለሁ ዛሬ አቅሜ አንተ ነህ አቤቱ እምነቴ እንደው አልታመነም አይተኸኛል በብዙ ግን እላለሁ አዝ፦ ሰላም ነው እላለሁ ያደረክልኝ ትናንትን እያየሁ ሰላም ነው እላለሁ በዚህ ኣይቀጥልም ክብርህን አያለሁ ሰላም ነው እላለሁ ያደረክልኝ ትናንትን እያየሁ ሰላም ነው እላለሁ ይህም ሌሊት ያልፋል ክብርህን አያለሁ ደህና ነው ካለች ሱንማይቷ የአንድ ልጇን ነፍስ ኣጥታ ከቤቷ ታድያ እንዴት አለኝ ሰላም ነው ባለቤት አለኝ የኔ አይደለሁም በትንሽ ትልቁ ብዙ ጭንቀቴ መልስ እንዳይሆነኝ ለዘመመው ቤቴ ተረድቻለሁ ይህንን አውቄአለሁ ነገሬን ሁሉ አስረክቤዋለሁ መኖሪያዬ የዘለዓለም አምላክ ያባቶቼ የነ ሙሴ ኣባት እንደ እግዚኣብሔር ያለ ማንም የለም የሚያውቅልኝ አንደአንተ አላገኝም ብታድነኝም ባታዳነኝም አንተ መልካም ነህ ይህንን አድርግ ያንን አታድርግ መች ትባላለህ ላደረራግህ ማስተካከያ ከማንም ኣትሻም ፍፁም በሥራህ ፍፁም በምክርህ አትሳሳትም ሰላም ነው (4x) ሰላም ነው (4x) አውጃለሁ ዛሬም መልካምንትህን ባልሞላው ነገሬ ስንፍና አልሰብክም ዕምነቴን አልጥልም ከንቱ ተናገሬ ከአንተ በላይ ለእኔ ለመጪው ዘመኔ እኔ አላውቅምና መቆዘሜን ጥዬ ይህም ያልፋል ብዬ ልለፍ በምሥጋና ብርቱ ሰልፍ ሲሆን ሕይወቴ እንድማር ነው አባቴ ነፋሱ ሲያይል ሲበረታ ድንቅህን ላይ ነው የማታ የማታ (2x) ብርቱ ሰልፍ ሲሆን ህይወቴ ለትምህርቴ ነው አባቴ ወጀቡ ቢያይል ሲበረታ ግን ድሉ የእኔ ነው የማታ የማታ (2x) ሰላም ነው (4x) ሰላም ነው (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection