Song Lyrics

የሮጡለትን ያዩታል

Hana Tekle
Yezelalem Fetari
ከአንተ በፊት የቆሰሉ ብዙ አሉ ለወንጌሉ እንደ እኔና እንደ አንተ በነጻነት ዘመን ያልተፈጠሩ ከአንቺ በፊት የተሰዉ ብዙ አሉ ለወንጌሉ እንደ እኔና እንደ አንቺ በነጻነት ዘመን ያልተፈጠሩ ከእኛ በፊት ብዙ አሉ የተሰዉ ለወንጌሉ እንደ እኛ በነጻነት ዘመን ያልተፈጠሩ ሳይሉ ችግሬን ጨርቄን ማቄን በጽድቅ የኖሩ በጌታ የተጉ ለጌታ የኖሩ በሰው የተጠሉ አቤት የሮጡለትን ያዩታል ከወደላይ የክብሩ ጌታ ሲያከብራቸው በሠማይ አቤት ያዩታል ጌታን ፊት ለፊት ሳያዩት ያመኑትን የናፈቁትን በነፍሳቸው የጨከኑት በሥጋቸው ያከበሩት አይገኝም አክሊላቸው በሠማይ ነው ክፍያቸው አቤት የሮጡለትን ያዩታል ከወደላይ ሆነው የባርነት ባሪያ ወጥተው ከሰውነት ተራ የእኔ የሚሉት የሌላቸው ልሩጥ ለእኔም ማያቃቸው ለወንጌል የቆሙ ለወንጌል የቀኑ ገንዘብ የማይደፍራቸው ሰልፍ ብርታታቸው አቤት የሮጡለትን ያዩታል ከወደላይ የክብሩ ጌታ ሲያከብራቸው በሠማይ አቤት ያዩታል ጌታን ፊት ለፊት ሳያዩት ያመኑትን የናፈቁት በነፍሳቸው የጨከኑት በሥጋቸው ያከበሩት አይገኝም አክሊላቸው በሠማይ ነው ክፍያቸው አቤት ያዩታል ጌታን ፊት ለፊት ማነው ታዲያ የዘምኔ አርበኛ ለጌታ ነገር ያልተኛ ብድራቱንስ ያልተቀበለ እውነት ለወንጌል የጨከነ በነጻነት ዘመን ራሱን የሰዋ ለጥቅም ያልኖረ በእምነቱ የጸና ማነው የዘምኔ ወንጌል ነጋሪ በተግባር የታየ የጽድቅ ተባባሪ ያልሆነ በፍፁም የነጻነት ባሪያ ከቶ ያልተገኘ እዚህ ሲሉት እዚያ ማነው የአቋም ሰው ዘመን ተሻጋሪ ሰልፍ እየበረታ ወንጌሉን ዘማሪ ማነው የዘመኔ ባለ አክሊል ተረኛ ለራሱ ያልኖረ ከሥጋው ጠበኛ ሞትን ጥቅሜ ብሎ በነፍሱ የጨከነ ግራ ቀኝ ያላየ ለቃሉ የታመነ ማነው የዘምኔ አርበኛ ማነው አቤት የሮጡለትም ያዩታል ከወደላይ የክብሩ ጌታ ሲያከብራቸው በሠማይ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection