Song Lyrics

ብቻ

Hana Tekle
Special Edition
በበደላችን ሙታን ሳለን ህያዋን ያረገን ዘላለም እንደ ኢየሱስ ያለ አዳኝ የለም የወለደን ዳግም የህይወት እንጀራ ሆነን ዉሃ ላይርበን ላይጠማን ከእንግዲህ ምስጋና ይድረሰው ለአብ ክብር ለእግዚአብሔር ልጅ በፀጋው ብቻ በእምነት ብቻ በኢየሱስ ድነናል ወደ አብ መግባት ሆኖልናል በፀጋው ብቻ በኢየሱስ ብቻ በእምነት ፀድቀናል ወደ አብ መግባት ሆኖልናል በመረቀልን በአዲስና ህያው መንገድ ቅዱሳን ተብለናል አሮጌው ሰውነት ተወግዶ አዲሱን ለብሰናል የመርገም እዳችን ከኛ ዘንድ የለም ተሽሯል በደሙ በመስቀሉ ስራ ሁሉን ፈፀመው ክብር ይሁን ለስሙ በፀጋው ብቻ በእምነት ብቻ በኢየሱስ ድነናል ወደ አብ መግባት ሆኖልናል በቃሉ ብቻ ለክብሩ ብቻ በኢየሱስ ድነናል ወደ አብ መግባት ሆኖልናል በሞት በትንሳኤው ከባርነት አውጥቶ ልጆቹ አድርጎናል የዘላለሙን ሞት በዘላለም ህይወት ለውጦታል ከቁጣ ልጅነት ተሰውረን ቀረብን በማዕዱ ዙሪያ በአብ ፊት ታየልን አዳኝ ኢየሱስ ከቅዱስ ማደሪያ በፀጋ ብቻ በእምነት ብቻ በኢየሱስ ድነናል ወደ አብ መግባት ሆኖልናል በፀጋ ብቻ በእምነት ብቻ በኢየሱስ ድነናል ወደ አብ መግባት ሆኖልናል በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ ከሞት ከእስራቱ እየተለየ ወገን ሆነው ኢየሱስ ለአለሙ ተቤዠው በስጋ በደሙ በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃን አየ ከሞት ከእስራቱ እየተለየ ቤዛ ሆነ ኢየሱስ ለአለሙ ተገኘ በስጋ በደሙ የኢየሱስ ነው ነፃ ያወጣል ስሙ ነው ለሕይወት ያበቃን እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ስም ከሰማይ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ኢየሱስ ኤልሻዳይ x2 መዳን በሌላ በማንም የለም x2 እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ስም ከሰማይ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ኢየሱስ ኤልሻዳይ x2 እናንተ ውስጣችሁ ያዘነ የሞት ፍርሀት ነፍሳችሁን የከደነ ይጣራል ኢየሱስ ዛሬም ወደ ሕይወት ግቡ ለዘላለም እናንተ ሸክማችሁ የከበደ በዚህ አለም ልባችሁ የወረደ ኑ ይላል ኢየሱስ ዛሬም ወደ እረፍቱ ግቡ ለዘላለም የኢየሱስ ስም ነፃ ያወጣል ስሙ ለሕይወት ያበቃል እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ስም ከሰማይ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ኢየሱስ ኤልሻዳይ x2
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection