ያየናል የማያይ ሲመስል ይሰማናል በብርቱ ዝም ሲል አለ የሚረዳን በዙፋኑ የሚደርስልን በማዳኑ /2×/ በድካማችን የሚራራልን የማይስቅ በውድቀታችን በሀዘናችን የሚያፅናናን ኢየሱስ አለ የሚያበረታን /2X/ እርሱ እራሱ እንደሰው ተፈትኖ ብዙ አልፎበታል ሰውን ሆኖ ከሐጥያት በቀር ብዙ ሆኗል የምንናልፍበት ይገባዋል /2X/ ይራራልናል ያስብልናል በጊዜው ሰርቶ ደግሞም ያስቀናል ይመጣል ነገ ዛሬም ያልፍና ደግሞ እንስቃለን ቆመን በትናንትና ደግሞ እንቆማለን በአዲስ ምስጋና በአዲስ ዝማሬ በአዲሱ ዜማ/2X/ ለጊዜው በሚያልፍ መከራ ብናልፍም ተራ በትራ የማይጥል ጌታን ይዘናል ልባችን በእርሱ ይፅናናል በፀጋው ስንቱን ተውጥተናል በወጅብ ሰላም ሆነናል ያልተወን ጌታ ይመስገን በእረፍቱ ከብቦ የያዘን ምንም ብናዝን በዚህ ዓለም ፈተና አይለወጥም ለእርሱ ያለን ምስጋና በመስቀሉ ያለፈውን እያየን በእምነታችን ዛሬም እንፀናለን ይራራልናል ያስብልናል በጊዜው ሰርቶ ደግሞም ያስቀናል ይመጣል ነገ ዛሬም ያልፍና ደግሞ እንስቃለን ቆመን በትናንትና ደግሞ እንቆማለን በአዲስ ምስጋና በአዲስ ዝማሬ በአዲሱ ዜማ/2X/ ጻድቅ ጌታ እንደሰው ተፈትኖ ብዙ አልፎበታል ሁሉን ሆኖ ከሐጥያት በቀር ብዙ ሆኗል የምናልፍበት ይገባዋል ይራራልናል ያስብልናል በጊዜው ሰርቶ ደግሞም ያስቀናል ይመጣል ነገ ዛሬም ያልፍና ደግሞ እንስቃለን ቆመን በትናንትና ደግሞ እንቆማለን በአዲስ ምስጋና በአዲስ ዝማሬ በአዲሱ ዜማ/2X/