በማይታለፍ ዘመን አለፍኩ በሰላም በዕረፍት ተከበብኩ በነውጥ ዘመን በሚሰጉበት ቤቴን ሞላኸው በራስህ በረከት በማይታረፍ ዘመን ማረፊያ የጭንቁ ዘመን ጥላ መሸሸጊያ ያንተ መንፈስ ነው ቅዱሱ መንፈስ ውስጥን የሚያርስ ለልብ የሚደርስ የሚሰማኝ በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራ ስጋት ያርፋል ብለኸኝ ይኸው አርፌያለሁ በስምህ እፎይ ብያለሁ የሚሰማኝ በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራ ስጋት ያርፋል ብለኸኝ ይኸው አርፌያለሁ በቃልህ እፎይ ብያለሁ በስምህ እኔ አርፌያለሁ በቃልህ እፎይ ብያለሁ ከትናንት ዛሬ ሰልፉ በርክቶ ሚሻል ሲጠበቅ ይባስ በርትቶ ደግ ቀን ርቆ ባረጀው አለም ሰው ካንተ ውጪ ተስፋም የለውም የሰላም ጥላ የእረፍት አምባዬ በክፉም ደና ቀን ማረፊያዬ ልቤን አርቀህ ሰላም ሰጠኸው ሀሩሩን ምድር እያለመለምከው የሚሰማኝ በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራ ስጋት ያርፋል ብለኸኝ ይኸው አርፌያለሁ በስምህ እፎይ ብያለሁ የሚሰማኝ በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ስጋት ያርፋል ብለኸኝ ይኸው አርፌያለሁ በቃልህ እፎይ ብያለሁ በስምህ እኔ አርፌያለሁ በቃልህ እፎይ ብያለሁ የሰላሙ ነፋስ ይነፍሳል በውስጤ አይገድበውም ቀን እና ለሊቴ የማግኘት የማጣት ጉዳዬ መቼም አይዝልም ሁኔታዬ ሰላሜ ኢየሱስ ትላንትም ዛሬ ህይወቴ ነህ የነፍሴ ዝማሬ ያገኘህ ከምንጭህ ይረካል እንደ ወንዝ ሰላሙ ይፈሳል ህልውናህ ህይወቴ ነው መገኘትህ እኔ አልችልም ከቶ ልኖር ያለ አብሮነትህ ያንተ መኖር ህይወቴን ወስኗል ልቤ አንተን አንተን ይላል ህልውናህ ህይወቴ ነው መገኘትህ እኔ አልችልም ከቶ ልዘልቅ ያለ አብሮነትህ ያንተ መኖር ህይወቴን ወስኗል ልቤ አንተን አንተን ይላል ልቤ ኢየሱስ ኢየሱስ ይላል ልቤ አንተን አንተን ይላል ልቤ ኢየሱስ ኢየሱስ ይላል