ፀጥታን ፈራን መስማትን ገፋን እኩል አወራን ማንም አልሰማን አልተሰማማን አደርን አደባባይ ለማይረባን ሲሳይ ከራስ ጋር ጠብ ገጥመን በጊዜያችን ፈርደን ባከንን ውስጥ ሳያርፍ ምን ቢጮሁ ከውስጥ ረብሽ ሳያመልጡ ከንቱ ድል ነው ግርግሩ የማያድን አጉል ጥሩ ጥፍት ከፀጥታ ሽሽት ከዝምታ ምን በጩኸት ቢያዋዙት አለ ችግር ቤት የማይቀርፉት አድምጥ ዝምታህን ስማ ፀጥታህን ዝም ስትል የሚያወራህን ዝግ ስትል የሚያረጋህን መድሀኒትህን አድምጭ ዝምታሽን ስሚ ፀጥታሽን ዝም ስትይ የሚያወራሽን ዝግ ስትይ የሚያረጋሽን መድሀኒትሽን በጥሞና ዘመን ሁከት በመንቃት ዘመን ባለ ፍዘት መንፈስ ቅዱስ አይለፍህ ግባ ከቤት ከምሽግህ ጥፍት ከፀጥታ ሽሽት ከዝምታ ምን በጩኸት ቢያዋዙት አለ ችግር ውስጥ የማይደርሱት አድምጥ ዝምታህን እግዚአብሔር ያለበትን ዝም ስትል የሚያወጋህን ዝግ ስትል የሚያረጋህን መድሀኒትህን አድምጭ ዝምታሽን ኢየሱስ ያለበትን ዝም ስትይ የሚያወጋሽን ዝግ ስትይ የሚያረጋሽን መድሀኒትሽን መፍትሄ ነው ፀጥታ መስጠት ለራስ ፋታ ማዳመጥ የውስጥን ማየት ያሉበትን ፀጥታን ጠላን ጩኸት ጠራን በሆታ ጠፋን ደጁ ውለን አደርን አድምጥ ዝምታህን ስማው ፀጥታህን አድምጭ ዝምታሽን መድኃኒትሽን ላድምጥ ዝምታዬን ልስማ ፀጥታዬን አድምጭ ፀጥታሽን መድኃኒትሽን