Song Lyrics

መዳኔ

Medane

የሕይወቴን ምዕራፍ ቀየረው ጌታዬ በደሙ አዎ በደሙ ክብር ይሁን ለስሙ የሕይወቴን ስርዓት ቀየረው ጌታዬ በሞቱ አዎ በደሙ ክብር ይሁን ለስሙ ሞት በሕይወት ተሸነፈ አለቅነቱ ተገፈፈ መውጊያው ከእጁ ተለየው የእግዚአብሔር ልጅ ገጠመው ሲኦል የታል ድል መንሳቱ የዘመናት ማስፈራቱ የትንሣኤው ጌታ ረታው የድል ንጉሥ የበረታው ክብር ይሁን በሞቱ ላነሣን የለምና ከዚህ በላይ መዳን ማምለጥ ሆነ ከሲኦል በረሐ አቤት በረከት የሰማይ ፍስሀ ማምለጥ ሆነ ከሲኦል በረሐ አቤት በረከት የሰማይ ፍስሀ ክብር ይሁን በደሙ ላነፃን የለምና ከዚህ በላይ መዳን ማምለጥ ሆነ ከሲኦል በረሐ አቤት በረከት የኢየሱስ ፍስሀ ማምለጥ ሆነ ከሲኦል በረሐ አቤት በረከት የሰማይ ፍስሀ ብርና ወርቅ በማይገዙት ብል ወይ ዝገት በማይበሉት ዘላለሜ ተጠበቀ ሞት በኢየሱሴ ወደቀ የስጋን ሞት ማልፈራበት ለዘላለም ምከብርበት መዝገብ አለኝ ከወደላይ ከምድሩ ጋር ማይተያይ ክብር ይሁን በሞቱ ላነሣን የለምና ከዚህ በላይ መዳን ማምለጥ ሆነ ከሲኦል በረሐ አቤት በረከት የሰማይ ፍስሀ ማምለጥ ሆነ ከሲኦል በረሐ አቤት በረከት የሰማይ ፍስሀ ክብር ይሁን በደሙ ላነፃን የለምና ከዚህ በላይ መዳን ማምለጥ ሆነ ከሲኦል በረሐ አቤት በረከት የኢየሱስ ፍስሀ ማምለጥ ሆነ ከሲኦል በረሐ አቤት በረከት የሰማይ ፍስሀ መዳኔ ይገርመኛል ይገርመኛል ይገርመኛል መዳኔ ይደንቀኛል ይገርመኛል ይገርመኛል መዳኔ ይደንቀኛል ይደንቀኛል ይደንቀኛል መትረፌ ይደንቀኛል ይደንቀኛል ይደንቀኛል ምስጋና ነው ያለኝ ምስጋና ለወለደኝ እንደገና አዎ እንደገና ክብር ይሁን ምስጋና ምስጋና ነው ያለኝ ምስጋና ሰው ላረገኝ እንደገና አዎ እንደገና ክብር ይሁን ምስጋና መዳኔ ይገርመኛል ይገርመኛል ይገርመኛል መዳኔ ይደንቀኛል ይገርመኛል ይገርመኛል መዳኔ ይደንቀኛል ይደንቀኛል ይደንቀኛል መትረፌ ይደንቀኛል ይደንቀኛል ይደንቀኛል ከዚህ በላይ ምን ይደንቀኛል ከዚህ በላይ ምን ይገርመኛል መዳኔ ይገርመኛል ይገርመኛል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection