Song Lyrics

ከሞት ባሻገር

Kemot Bashager

ተስፋ እንደሌላቸው በምሬት እኛ አናዝንም በስጋ ከምንወዳቸው መለየት በእርግጥ ቢያምም የዘላለም ተስፋ አለን ከሞት ወዲያ በዚያ እንገናኛለን በንጉሥ ማደሪያ ተስፋ እንደሌላቸው በምሬት እኛ አናዝንም በስጋ ከምንወዳቸው መለየት በእርግጥ ቢያምም የዘላለም ተስፋ አለን ከሞት ወዲያ በዚያ እንገናኛለን በኢየሱስ ማደሪያ የቅዱሳን ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው ይህንን ክብር የሚያገኝ ሰው ማነው? በእርግጥ ቢለይም ከወዳጆቹ ከዚህኛው አለም ኢየሱስ አለ የተቀበለው ለዘለዓለም የፃድቁ ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው ይህንን ክብር የሚያገኝ ሰው ማነው? ሲሄድ ቢለይም ከወዳጆቹ ከዚህኛው ዓለም ኢየሱስ አለ የተቀበለው ለዘለዓለም አለኝ ቤት አለኝ-አለኝ በሰማይ አለኝ ቤት አለኝ-አለኝ በሰማይ በእጅ ያለተሰራ-የሰማይ ሀገር አለኝ መኖሪያ- ከዚህ ስሻገር አለን ቤት አለን-አለን በሰማይ አለን ቤት አለን-አለን በሰማይ በእጅ ያለተሰራ-የሰማይ ሀገር አለን መኖሪያ- ከሞት ባሻገር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection