Song Lyrics

ኃይሌም

Hailem

በይሁን ብቻ በቃልህ ብቻ ሰማይ ምድሩ ቀና የስምህ ጉልበት የኃይልህ ችሎት ሁሉን አፀና የሰው ክንድ የአንተን አይቋቋምም ከቶ ችሎ አትገመትም አትጨረስም እንዲህ ነህ ተብሎ ምን ቢሰበሰብ ኃይል ቢመስል ሲታይ የሚያይል አንተን ያመነህ ግን አይወድቅም ካንተ ማንም አይቀድምም የምድሩ ኃይል ተጠቅጥቆ ቢያሰፈስፍ ሊታይ ልቆ የፈጠርከው አይገዛህም! ኃይል ያንተ ነው አይቻልም! በስብርባሪ ደህና የደረሰ አለ ባንተ ጉልበት ደሞም በጠጠር ኃያሉን ጥለህ አየን እንደዘበት አበቃ ሲባል ያንተ ይጀምራል ያለገደብ ከልካይ የለህም! ካሰብክ ልትሰራ አትወሰንም! ምን ቢሰበሰብ ኃይል ቢመስል ሲታይ የሚያይል አንተን ያመነ ግን አይወድቅም ካንተ ማንም አይበልጥም የምድሩ ኃይል ተጠቅጥቆ ቢያሰፈስፍ ሊታይ ልቆ የፈጠርከው አይቀድምህም! ካንተ ማንም አይበልጥም! የኔ ኃይል ጥቂት ትንሽ ቢሆንም የዙሪያዬ ድምፅ ጉልበት ቢያይልም ያመንኩትን ክንድ ግን የለም ሚያክለው አልናወጥም ኃይል የእግዚአብሔር ነው እርሱ የዘጋውን የሚከፍት የለም የለም ሚዘጋ የከፈተውንም ብርቱ ክንድ አለው የማይለካ የታመኑትን የማያስነካ ብርቱ ክንድ አለው የማይነካ የታመኑትን የማያስነካ ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው የኔ ጉልበት ሰማይና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው! ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው! ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው! ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው!
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection