Song Lyrics

እውነትና እውነት

Hana Tekle
habte Semay
በሰው ክፋት ማዕበል ምድር ስትናወጥ ፈጣሪ እንኳን በሰራው ፍጡር እስኪጸጸት የአንድ ኖህ ጎዳና አካሄድ ቢቀና የሰው ህይወት አልቀጠለም ወይ እንደገና በውሸት ከተማ እውነት እንግዳ ነው መስሎ ጸጉረ ልውጥ የሚያውቀው ሞኝ ነው እውነትን በተቀማ ትውልድ ማን ይሆን የእውነት ዘመድ ሁሉ ገሸሽ ሲል የአመጽ ቤት ሲደራ ማን አብሮ ይዘልቃል ከባይተዋር ጋራ እንደውሃና ዘይት አይደሉም ወይ እውነትና ሃሰት ምን አንዱ ቢበዛ መቼም አያብሩም ዘላለም በርቀት በጊዜም ፈተና ወደቅክ ሚለው የለም በእሳት ንዳድ አልፎ አመድ አያውቀውም በልዩነት መንገድ በሰላም ይተማል አጃቢ ሳያሻው ዘላለም ይኖራል የዝምታው ድምጸት ከመብረቅ ጽኑ ነው አለት ከሚያነቃ ከሚሰነጥቀው እርሱ ተረጋግቶ ሀገር ይረበሻል የለህም የሚለው እንቅልፍ አጥቶ ያድራል ከብዙ ግርግር አባይ ከዋለበት እውነት ከሚመስል አሳች ከበዛበት ዘንድሮም ጉዳዩ ከእውነት ጋር ብቻ እውነትና እውነት ከራሱ ጋር ብቻ በውሸት ከተማ እውነት እንግዳ ነው መስሎ ጸጉረ ልውጥ የሚያውቀው ሞኝ ነው እውነትን በተቀማ ትውልድ ማን ይሆን የእውነት ዘመድ ሁሉ ገሸሽ ሲል የአመጽ ቤት ሲደራ ማን አብሮ ይዘምታል ከባይተዋር ጋራ የታመነ ጓዳው ዮሴፍ ትንሹ ዛፍ ባልዋለበት ቢውል በእመቤቲቱ አፍ ከእመቤትስ በላይ ሹምስ ማንን ያምናል በሃጥእ ዘመን ዘንድ ጻድቅ ወህኒ ይወርዳል ምን ቢታፈን ሃቁ በሚያልፍ ባለጊዜ በማያልፍ ተክሷል ደርሶ የእውነት ጊዜ ባደባባይ ቢያፍር እውነትን አንግሶ ክብሩም ባደባባይ ይኸው ተመልሶ ሀብት ነው ጌጥ እውነት ምን ቢያጡም ለጊዜው ከርሞ ሚመነዘር ከፋይ ለከፈለው እውነትን በተቀማ ትውልድ ማን ይሆን የእውነት ዘመድ ብርሃን ቃሉን ሲሰጥ ጨለማን ሲደክመው የእውነት ቤት ይደምቃል ለ እግዚአብሔር ያደረው ጽኑ ጽኑ ጽኑ ጽኑ ጽኑ ጽኑ እውነት እግዚአብሔር ነው የማይለውጥ ጽኑ በሰልፍ ብዛት የማይደክመው ከበረታው በላይ ብርቱ ባህሪው ሰላም ነው አያምንም በሁከት ራሱን ለማሳመን አይገባም ከጭንቀት ህሊና ወዳጁ ጊዜ መፍቻ ቁልፉ ተረጋግቶ ይኖራል ተከድቶ በስንቱ ጽኑ ጽኑ ጽኑ ጽኑ ጽኑ ጽኑ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection