Song Lyrics

ብቻ ልቤን

Hana Tekle
habte Semay
አንደበትህ ይታክታል የሆድን ሁሉ ቢናገር ለመጣው ለሄደው ሁሉ የሚያልፍበትን ቢዘረዝር የሰሚም- የሰሚም ጆሮ ይዝላል ለጊዜው ለሰሞንም ቢያዝን ብቻ ልቤን ደግፈው አልፈዋለው ብርቱውን ቀን ብቻ ልቤን ደግፈው አልፈዋለሁ ክፍውን ቀን እጠራሃለሁ በስምህ ውስጥ ሰላም አለ እጠራሃለሁ በስምህ ውስጥ ብርታት አለ በስምህ ውስጥ እግዚአብሔር በስምህ ውስጥ እረፍት አለ በስምህ ውስጥ ጽናት አለ በስምህ ውስጥ ሰላም አለ በስምህ ውስጥ ከፀሓይ በታች መልስ ባጣሁለት ጉዳይ ቢያይልም ግርታዬ አይኔን ተክያልህ ሰማይ ከያዘኝ ከከበበኝ በላም አንተን አምንሃለሁ ብቻ ልቤን ደግፈው አልፈዋለው ብርቱውን ቀን ብቻ ልቤን ደግፈው አልፈዋለሁ ክፍውን ቀን ልቤ ተጠብቆ በሚሆነው ነገር እታገስሃለሁ አለህ አንድ ነገር ብቻ ልቤን ጠብቀው አልፈዋለው ብርቱውን ቀን ብቻ ልቤን ደግፈው አልፈዋለሁ ክፍውን ቀን በስምህ ውስጥ ሰላም አለ በስምህ ውስጥ እረፍት አለ በስምህ ውስጥ ጽናት አለ በስምህ ውስጥ ልብ ብቻውን ሲቀር በሃሳብ ሲወረር በሁነኛ ነፋስ በማዕበል ሲሰወር ደጋፊ ከሌለው ማን ከማን ያስጣል ልብ የወደቀ ቀን ለሞት እጅ ያሰጣል ልቤን የሚታደግ ብርቱ ግንብ አለቴ አጥር ሃይሌ ስምህ ነው የተስፋ ጽናቴ አንተ ነህ እግዚአብሔር ጽኑ መታመኛ አደራ የምለው አንተን ነው የልቤን መገኛ በስምህ ውስጥ ሰላም አለ በስምህ ውስጥ እረፍት አለ በስምህ ውስጥ ጽናት አለ በስምህ ውስጥ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection