ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖረ ልቡ ስለመንጋው ያደረ ለአንዲት ምስኪን ነፍስ ግድ እያለው ብዙ አሉኝ ብሎ አንዷን የማይተው ይሄዳል ያለእረፍት ሁሉ ጋ የጠፋችውን ያቺኑ ፍለጋ ሲያገኛት ሌላ እንደሌለው ደስታው መለኪያም የለው የባዘነውን የሚመልስ የጠፋውን የሚፈልግ የተሰበረውን የሚጠግን የሚያጸና የደከመውን ይህ ነው የእኔ እረኛ ይህ ነው የእኔ መዳኛ ይህ ነው የእኔ መጽናኛ ኢየሱስ መልካሙ እረኛ መታመኛዬ መጠገኛዬ መደገፊያዬ መታደጊያዬ ጠያቂ አለኝ ጠያቂ ፈላጊ አለኝ ፈላጊ ጠያቂ አለኝ ጠያቂ መሽቶም ሲነጋ ጠባቂ ይህ ነው የእኔ መጽናኛ ኢየሱስ መልካሙ እረኛ፡፡ ውዴ የሚታደገኝ ራሱን ሰጥቶ የሚያውቀኝ ከልብ በስም ለይቶ ለአፍታም ለቅጽበት አይለየኝ ለሚሰማሩብኝ አይተወኝ የእረኞች አለቃ እረኛዬ የገዛኝ በፍቅር መጋቢዬ ኢየሱስ የነፍሴ አባት ጠባቂዋ ከዱር ከገደሉ ማምለጫዋ የባዘነውን የሚመልስ የጠፋውን የሚፈልግ የተሰበረውን የሚጠግን የሚያጸና የደከመውን ይህ ነው የእኔ እረኛ ይህ ነው የእኔ መዳኛ ይህ ነው የእኔ መጽናኛ ኢየሱስ መልካሙ እረኛ መታመኛዬ መጠገኛዬ መደገፊያዬ መታደጊያዬ ጠያቂ አለኝ ጠያቂ ፈላጊ አለኝ ፈላጊ ጠያቂ አለኝ ጠያቂ መሽቶም ሲነጋ ጠባቂ ይህ ነው የእኔ መጽናኛ ኢየሱስ መልካሙ እረኛ