Song Lyrics

ሩጫው

Hana Tekle
habte Semay
ሩጫው አይደል ወይ ሰላምን ፍለጋ እርካታን ፍለጋ ሁሉም በየፊናው ሚለው ደፋቀና ሚለው ጎንበስ ቀና ገንዘብ ቁስን እንጂ እረፍት መች ይገዛል በየደረሰበት ሰው ሃሳብ ይገዛል ጭንቀት ይሸምታል እረፍት መገኛው ኢየሱስ ሰላም ማደሪያው ኢየሱስ ደስታ ሀገሩ ኢየሱስ እረፍት መኖሪያው ኢየሱስ ሀብት ጥሪት ይዞ የተትረፈረፈ ከእድሜ ልክ ያለፈ ሰላም ከሌለበት ሰላምን ፍለጋ ስንቱ ነው የዋለ የተንከራተተ ዛሬን እረፍት አጥቶ ለነገ ያልማል ነገም ነገን ሲቀርጽ ሳያልቅ ዘመን ያልቃል እረፍት መገኛው ኢየሱስ ሰላም ማደሪያው ኢየሱስ ደስታ ሀገሩ ኢየሱስ እርካታው መኖሪያው ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ በላው ጠጣው ትርፌ ምንድነው? አጌጥኩ ለበስኩ ትርፌ ምንድነው? ተማርኩ አወኩ ትርፌ ምንድነው? ምድር ሞላልኝ ትርፌ ምንድነው? ኸረ እኔ በእንጀራ ብቻ ኸረ አልኖርም ኸረ እኔ በምድሩ ብቻ ኸረ አልኖርም ክፍተቴ ሌላ ነው ጉድለቴ የማልሞላው በማንነቴ እሮጬ እሮጬ ትርፌ የኔ ድካም ነው የነፍስ እርካታዬ ጌታ ባንተኮ ነው እንኳን ያንተ ሆንኩኝ አወኩህ እንኳን እንዳልችል ሆኛለሁ ለሌላ እንዳልሆን የማምነው እውነት በፍቅር ይዞኛል ሌላ ሌላ እንዳላይ ውስጤን ሞልተኸዋል አሰብኩት እራሴን ካንተ ውጪ አሰብኩት ወጥቼም ከቤትህ ባዶ ነኝ ቅብዝብዝ የሌለኝ እረፍት እኔ አልችልም ሰው አልሆንም በሌለህበት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection