Song Lyrics

ሃብተ ሰማይ

Hana Tekle
habte Semay
አዲስ ሰማይ አዲስ ምድር የብርሃን ሀገር የብርሃን ቅጥር ምርአፍ ተዘግቶ ምርአፍ ሲጀመር አየዋለው ያኔ በድል በክብር ሲያልፍ ፊተኛው ሰማይ ደግሞ አንደገና አዲስ ሰማይ ሲያበቃ ይሄኛው ምድር ዘለዓለም አለ የክብር ምድር (፪x) ጨለማ ዳግም በማይሰፍነበት ፀሐይም ጨረቃም በሌሉበት በጉ ብርሃን ነዉ ያበራል ሀገር በክርስቶስ ይደምቃል ሀብተ ሰማይ ፅኑ ተስፋዬ የዘለዓለም መኖርያዬ ሀብተ ሰማይ የክብር ተስፋዬ ከአየሱስ ጋር ለዘላዓለም መንገሻዬ አይን ያላየው ጆሮም ያልሰማው ጌታ ለሚወዱት ያዘጋጀው ልብሳቸውን በበጉ ደም ላጠቡ የሰፋውን መንገድ ጥለው ለዘለቁ ሀብተ ሰማይ ፅኑ ተስፋዬ የዘለዓለም መኖርያዬ ሀብተ ሰማይ የክብር ተስፋዬ ከአየሱስ ጋር ለዘላዓለም መንገሻዬ በተስፋ ድንበር በፍቅር ሀገር የእምነት ፅናት ምላሽ ሲሰምር ሲበሰር የዘለዓለሙ ደስታ የታመኑት የናፈቁት ላይም ሲበቃ ሀብተ ሰማይ ፅኑ ተስፋዬ ከአየሱስ ጋር ለዘላዓለም መኖርያዬ ሀብተ ሰማይ ፅኑ ተስፋዬ ከአየሱስ ጋር ለዘላዓለም መንገሻዬ ሌት በማያውቀው የቀን ጅረት ብርሃን ውሎ ብርሃን ማደር ምናለ ደስታ ምናለ ውበት ከክርስቶስ ጋር ነግሶ አንደማየት ሞት በማይገጥመው የህይወት ጅረት ድል ከነሱት ጋር ተካፍሎ እርስት ምናለ ውበት ምናለ ፍሰሃ አንደመገኘት ከዚህ ክብር ጋር ሲያልፍ ፊተኛው ሰማይ ደግሞ አንደገና አዲስ ሰማይ ሲያበቃ ይሄኛው ምድር ዘለዓለም አለ የክብር ምድር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection