ፊደል ተግጣጥሞ የቱ ቃል ገለጠህ ቃላት ተሰካክተው ምን ቢባል ተረከህ ያንተን ልክ አዋቂ አንተ እግዚዓብሔር ብቻ እራስህ ንገረኝ ምን እንድልህ ብቻ የተባልከው ሁሉ ካንተ በታች ሆኗል ለፍጥረት ሚበዛው ላንተ አቅም አንሶታል ያንተን ልክ አዋቂ አንተ እግዚዓብሔር ብቻ እራስህ ንገረኝ ምን እንድልህ ብቻ መጀመርያም መጨረሻም የሌለህ አልፋ ኦሜጋ ፊተኛም ሗለኛም የሌለህ እግዚዓብሔር አንተ ነህ ፪ የኔ ትልቅ አንተ ነህ የኔ ጀግና አንተ ነህ ሁሉን በስርህ አስተዳዳሪ በላይ ለሁሉ ሁሉን ፈጣሪ የግዙፍ ግዙፍ የትልቅ ትልቅ ቃል በማይደፍረው የከፍታ ጥግ አንተ እግዚዓብሔር አንተ ብቻ ነህ ትልቅ መሳዩን ትንሽ ያደረግህ ጀግና መሳዩን ያንበረከክህ ጠቢብ መሳዩን ሞኝ ያደረግህ ያለው መሳዩን ባዶ ያደረግህ የለም ያሉህ የሉም ዛሬም የሚሉህ ነገ አይኖሩም ፪x ይገርመኛል ትጋታቸው የከንቱነት ጥበባቸው ካንተ ውጪ ህይወት ማሰባቸው አንተው ባበጀኸው አእምሮ ባንተ ጥበብ ተቀምሮ እስትንፋስ ለግሰህ በእፍታህ ባምሳልህ ሰርተኸው ስታበቃ የለህም የሚልህ ማን ነው እኮ የለህም የሚልህ ማን ነው ለመኖርህ የሱም መኖር ምስክር ነው ፫ ለመኖርህ የኔም መኖር ምስክር ነው ሉዓላዊነት ከጥንት ከዓለማት በፊት የነበረ አለህ የለህም ቢባል ከመኖር ያልተገደበ እግዚዓብሔር አለህ በማደርያህ እግዚዓብሔር አለህ በዙፋንህ አለህ በማደርያህ አለህ በዙፋንህ