Song Lyrics

በሩን ክፈቱ

Hana Tekle
habte Semay
ከስም ሁሉ በላይ ኃያል ስም አለው በዚህ ስም አምነን ድነናል ይኸው ምስክሮቹ ነን ሕይወት ደርሶናል ሰማይ ሲጎበኘን ለዓለም በርተናል ተጠቅልለናል በክርስቶስ በኃያሉ ስም ከነበርንበት ዓለም የለንም የሚበልጥ አይተን የሚደንቅ ክብር ሰውን ኑ እንላለን አልፈን ከምድር አምላክ ስጋ ሆነ ለኛ ማለደ ከአብ አስታረቀን ስርየት ወረደ ሕያው ልጆቹ ነን ዳግም ወልዶናል ዘላለም ሲያገኘን ከሞት ጠፍተናል ተጠቅልለናል በክርስቶስ በኃያሉ ስም ከነበርንበት ዓለም የለንም የሚበልጥ አይተን የሚደንቅ ፍቅር ሰው እንጋብዛለን ወደዚህ ክብር እናንት መኳንንቶች በሩን ክፈቱ የክብር ንጉሥ ይግባ በሩን ክፈቱ ይሄ ንጉሥ ማነው? እሱ እግዚአብሔር ነው የክብር ሁሉ ጌታ? እሱ እግዚአብሔር ነው የክብር ሁሉ ጌታ የክብር ሁሉ ገዢ እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኃያል የሰማይ የምድሩ የልዑላን ጌታ እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኃያል ሆሆ ኃያሉ እግዚአብሔር እሱ እኛን ጎበኘ እንድንዘምርለት ዙሪያው ሰበሰበን ሆሆ እግዚአብሔር ረዳን እግዚአብሔር አሰበን በየደረስንበት ኃያል መዝሙር ሆነን ምስጋና የተገባው እሱ ነው ውዳሴ የተገባው እሱ ነው ለኛ ታየን መድኃኔዓለም እንደሱ የለም ዘለዓለም ለኛ ተገለጠ መድኃኔዓለም እንደሱ የለም ዘለዓለም ዝማሬ የተገባው እሱ ነው ስግደትም የተገባው እሱ ነው ለኛ ታየን መድኃኔዓለም እንደሱ የለም ዘለዓለም ለኛ ተገለጠ መድኃኔዓለም እንደሱ የለም ዘለዓለም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection