Song Lyrics

ተናገር

Hana Tekle
habte Semay
ባነበብን ቁጥር ባወቅነው የማንለምደው ቃልህን በገባን ቁጥር ባወቅነው ምንፈልገው ቃልህን ነው ዛሬም እንድትልልን ሳይሆን ልትል ያሰብከው ያግኘን ያለመከልከል ተናግረህ ያለገደብ ሥራብን መንፈስህ ይግዛን ይስፈንብን በሙላት የልብህ አሳብ ያጥምደን የሚያቆመን ያ ነው በጽናት እናድጋለን እንጂ ሰርክ ወደ አንተ ልናድግ አይቻለንም በአንተ ላይ ከፍለን ባወቅንህ ቁጥር ዝግ እንበል እንይ ወደላይ ምን ብናውቅ ጥበብ ቢጠጋን ሲመስለን ያወቅን የበቃን አናውቅም ባወቅንህ ቁጥር ደቀመዝሙር ነን ሁሌ በአንተ ሥር ተማሪዎች ነን ሁሌ ልጆችህ መቼም በማንጨርሰው ትምህርትህ ከፍለን ባወቅንህ ጥቂት ትሑት አድረገን ባንተ ፊት ታማኝ አድረገን ለቃልህ አብቃን ለውድ አሳብህ መስታወት በሆነው ቃልህ አንቃን በውድ መንገድህ ተናገር ኢየሱስ ተናገር በኃይል እንሰማሃለን ተናገር መንፈስ ቅዱስ ተናገር በሙላት እንሰማሀለን ተናገር እንሰማሀለን ተናገር እንሰማሀለን ባነበብን ቁጥር ባወቅነው የማንለምደው ቃልህን በገባን ቁጥር ባወቅነው ምንፈልገው ቃልህን ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection