ሊያገለግልህ የጠራኸው በሕዝብህ ፊት የሾምከው ስንቱ ርቆህ ያገለግላል ለራሱ ክብር አድሮ ይውላል ስንቱ ርቆህ የራሱን ክብር ያገለግላል ለዝናው ስሙ ታግሎ ይኖራል፡፡ ያላንተ ጉዞ ስም ዝናን ብቻ ይዞ የሥጋ ጥረት በሌለህበት ያለአንተ ክብር በእኔነት ፍቅር በጸጋ ካባ ለራስ ወከባ ለከንቱ መንገድ ባንተ ሲነገድ ፍለጋ ክብርን ፍለጋ ዝናን ፍለጋ ብልጫን ፍለጋ ፍለጋ ንዋይን ፍለጋ ትኩረትን ፍለጋ ፍለጋ አምልኮተ ዝና አምልኮተ እኔ በአምልኮ መልክ ሽፋን በፍቅሬ ተይዤ በንጉሥ ዙፋን ላይ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ በውድድር መንፈስ ምስባክ ለታይታ በትወና ህይወት የእኔ ለእኔ ዋይታ ፍለጋ ክብርን ፍለጋ ዝናን ፍለጋ ብልጫን ፍለጋ ፍለጋ ንዋይን ፍለጋ ትኩረትን ፍለጋ ፍለጋ በሌለህበት ሳውልህ ለዝና ስሜ ስፈልግህ ተላላ የልቤን ባያገኘው ካንተ ማን ሊሰውረው ከባዶ ጩኸት ከሌለህበት ዝምታዬ ካገነነህ ባለህበት ክብሬ ያ ነው ያከበረህ እኔነቴን የሰበረ ፍለጋዬ ይሁን ለጉዳይህ ፍለጋዬ ይሁን ለሐሳብህ ፍለጋዬ ፍለጋዬ ይሁን ለክብርህ ስራዬን ትመዝናለህ ከመንበርህ ታየኛለህ ፍለጋዬን አጥራው መንገዴን ላረካ የቆምኩለትን የራስ ጥሜን መከሩ ብዙ ነው ሥራ አለ በቤቱ ወደሞት የሚነዳ አለ በየዕለቱ በራስ ፍቅር ታመን መሽቶብን ይነጋል ኢየሱስን ሳያይ ስንቱን ሞት ይቀድማል እድሜአችን ቢበዛ ሰባ ነው ቢያልፍ እንኳን ሰማንያ ምን አለን ክብር ምን አለን ንዋይ ኢየሱስ ከአንተ ወዲያ ምን አለን ዝና ምን አለን ክብር ኢየሱስ ከአንተ ወዲያ