Song Lyrics

በታሪክ

Hana Tekle
habte Semay
ክቡር የሰው ልጅ ክቡር በሰማይ በምድር የአንድ ዘር ቅጂ የአንድ ነፍስ ስፍር አሻራ መልኩ ቢለይ ቀለሙ ወርቁ ሲፈተሽ አንድ ነው ደሙ ከጎሳ ከዘር ከባህል ትውፊት ከሀገርም በላይ ከብሄር በፊት አብ የፈጠረው በሁሉ አንግሶ ወልድ የሞተለት ደሙን አፍስሶ ሰው ነው ክቡር ሰው የተከበረ በአምሳለ እግዚአብሔር የተመተረ ምኑን ቢለያይ ድንበር አብዝቶ አንድ አድርጎታል ክርስቶስ ሞቶ ክቡር ክቡር ክቡር ክቡር ክቡር ክቡር ክቡር ክቡር ፍጡር ክቡር ክቡር ክቡር በታሪክ ማይገናኘውን የታሪክ ልዩነት ያለውን የዘር የዳር ድንበር ያበጀውን በምንም በምንም ጭራሽ ማይገጥመውን ኢየሱስ በታሪክህ አንድ አደረግከው በታሪክህ አገናኘኸው በመስቀልህ አንድ አደረግከው በመስቀልህ አገናኘኸው አንድ ነን ማለትን ቻለ ከእኔ በላይ ለአሳር ያለ ክርስቶስ በመስቀልህ የስንቱ ልብ ተቀየረ ምሳሌ ሆንከው ለፍቅር አሳየኸው ዝቅን ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ሆነህ ሳለህ ፈቅደህ መገፋትህን አሳየኸው የፍቅርን ልብ እኔነቱን አስወገድከው በታሪክህ አሸንፈህ ታሪኩን ከንቱ አደረከው በታሪክህ አንድ አደረከው በመስቀልህ አገናኘኸው ጨዋ የለም ባሪያ የለም ጉራማይሌውን አንድ አደረግህ ማይገናኘውን አገናኘህ ህዝብ ልጅ አንተ አባት ተባልህ ህዝብ ልጅ አንተ አብ አባት ተባልህ ጉራማይሌውን አንድ አደረግህ ማይገናኘውን አገናኘህ ህዝብ ልጅ አንተ አባት ተባልህ ህዝብ ልጅ አንተ አብ አባት ተባልህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection