Song Lyrics

ረግቻለው

Hana Tekle
habte Semay
ለሰላሜ ሚሆነኝን አውቂያለሁ አግኝቻለሁ ለእፎይታዬ ሚበጀኝን አምኛለሁ ተቀብያለሁ የእግዚአብሄር ልጅ በርቶልኛል በመንፈሱ ረግቻለሁ ላልወሰድ በምድር ተረት ለዘላለም ታትሜያለሁ ከአለም ዋኖች በተሰወረ ከጠቢባን ዘንድ ባልነበረ የሞኝነት በሚመስል ታምር አርፍያለሁ ባንተ ማመን ሚስጥር የማይነጥፍ ነው ሰላሜ የማያርፍ ነው እረፍቴ ማደርያህ ልሆንህ ፈቅደህ ገብተሃልና ከህይወቴ የማይደበዝዝ ፍቅርህ ነው ሽንገላም ወረትምበሌለው ካንተ ያልተቀበልኩት ምን አለኝ ቀረ ምለው?? ባንተ ደስ ብሎኛል ጸጋህ በዝቶልኛል ረክቻለሁ አመሰግናለሁ ሰላም ረግቶልኛል ፍቅር ዘልቆልኛል ረግቻለሁ እባርክሃለሁ በሰማያዊው በረከት በራስህ ተባርክያለሁ እዚህ እንዳልናወጥ ከእቅፍህ ገብቻለሁ አልሸበርም በአለም በሚሰማው ክፉ ወሬ ባለኸኝ ረግቼ አለሁ በያዝከኝ እስከዛሬ አንተን ሰጥተኸኛል አንተን ሞልተኸኛል ረክቻለሁ አመሰግናለሁ አንተ ሞልተኽኛል ህይወት በዝቶልኛል ተባርክያለሁ ልጅህ ተብያለሁ አንተን ይዞ ያልረካ ማነው አንተን ይዞ ያልሰከነ ማነው አንተን ይዞ የባከነ ማነው አንተን ይዞ የባዘነ ማነው እኔ ረክቻለሁ ሰላም አግኝቻለሁ ረግቻለሁ አመሰግናለሁ ለበዛልኝ ሰላም ለበዛልኝ ፍቅርህ ለበዛልኝ ህይወት ለበዛ ምህረትህ ይብዛልህ ክብር ይብዛልህ ሞገስ ይብዛልህ ክብር እየሱስ ይብዛልህ ሞገስ ይብዛልህ ምስጋና ይብዛልህ ክብር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection