ከነገር ጅማሬ ፍጻሜ ይልቃል ቀን ሳለ ጎበዝ ከየት እንደወደቀ ያስባል የጅማሬ ውበት የዳነበቱ ደብዝዞ ሳያልቅ በመንገድ ከንቱ በጸጋ ሽፋን ፋኖ ተማምኖ ስቆ ለውሃ ብዙ አለና የቀረ ባክኖ አልፈልገውም ለብታዬን እግሮቼን አድስ እኔ አልሻም መባከን በልማድ መደንዘዝ ግታው ሰበቤን ያደከመኝን ሰበብ በኩሬን የሚያስንቀኝን ግታው ምክኒያቴን የተጫነኝን ምክኒያት በኩሬን የሚያስጥለኝን፡፡ መሀል ሰፋሪ እዚህም እዚያም ሁሉ አይቅርብኝ አገም ጠቀም የለብታ ወንዝ ከባድ ፈተና ወይ ያልበረደው ወይ እሣት ያልገባው ገና አቋም በሌለው ከከልካይ ማዶ በነፃ ክልል ይነጉዳል ፈቅዶ፡፡ ግታው ሰበቤን ያለዘበኝን አክብጄ እንዳልይዝ ያጠመደኝን ግታው ምክኒያቴን የታገለኝን ለሁለት ጌቶች ያሰለፈኝን ነግቶለት ሕይወት ጉዞ ጀምሮ በአንተው ምሕረት በስም ተምሮ ከመንከራተት ተርፎ ያልተረፈ ዛሬም የሚባክን ልቡ ያላረፈ ገና! ዳግም ባርነት ዳግም እስራት ባልሰከነች ነፍስ ልጓም በሌላት፡፡ ይብቃኝ ምክኒያቴ የተጫነኝ አጥብቄ እንዳልይዝ ያታገለኝ ግታው ምክኒያቴን ያደከምኝን ትጥቄን ያላላ ያለዘበኝን በመንፈስ አንቃኝ አዚሜን ገፍፈህ የታገትኩበትን ገመዴን ፈትተህ ግታው ሰበቤን ያበረታኝን ለሁለት ጌቶች ያሰለፈኝን