ውጣ ውረድ ቢበዛ እንኳን ቢጨንቀኝ የማደርገዉ አንተን ትቼ ሌላ አማራጭ መፈለግ አይሆንልኝም ውላችን አይደለም ስኬት ሳይሆንልኝ ግን ልርቅህ በደምህ የተዋጀሁት በቂዬ ነው ማንነትህ አዝ:- የወደድከኝ ጌታ አከበርኩህ ጌታ ነፍሴም ተሰጥታለች ለአንተ ታዚም ሁሌም ጠዋት ማታ ቃልኪዳናችንም ዘለዓለማዊ ነው አጋጣሚ አይደለምና ፍቅርህ ሁኔታ ላይ ያየሁህ አንለያይም (8x) ሄድኩኝ ብለው ከሄዱበት አንዳች የለም የተረፈ ዛሬ ታይቶ ከሚጠፋው ከዚች ምድር ያለፈ ዛለዓለሜ ቤቴ የአንተ ይሁን ይህን እወዳለሁ በከንፈሬ ሳልበድልህ አንተን ብቻ መርጫለሁ አዝ:- የወደድከኝ ጌታ አከበርኩህ ጌታ ነፍሴም ተሰጥታለች ለአንተ ታዚም ሁሌም ጠዋት ማታ ቃልኪዳናችንም ዘለዓለማዊ ነው አጋጣሚ አይደለምና ፍቅርህ ሁኔታ ላይ ያየሁህ አንለያይም (8x) የአንተ ብሆን መታደሌ የጌታ ልጅ መባሌ ተጠርቼ መች ቀረሁኝ አባ በአንተ ተወደድኩኝ ምን አጥቼ ልሂድ ከአንተ ምን ጐድሎብኝስ ከእቅፍህ የእኔ ብዬ ምኖርበት መመኪያዬም ጌጤም ቤትህ አዝ:- የወደድከኝ ጌታ አከበርኩህ ጌታ ነፍሴም ተሰጥታለች ለአንተ ታዚም ሁሌም ጠዋት ማታ ቃልኪዳናችንም ዘለዓለማዊ ነው አጋጣሚ አይደለምና ፍቅርህ ሁኔታ ላይ ያየሁህ አንለያይም (፲6x)