Song Lyrics

ሞትክልኝ መድህኔ

Hana Tekle
Agizegn
ስፍራን አዘጋጅተህ እኔን ከጠራኀኝ በክብር እንድኖር ወደኅኝ ከአዳንከኝ ከእስትንፋሴ ይልቅ ቀርበኀኛልና ውዴ ተቀበለኝ የልቤን ምሥጋና አዝ:- በዋጋ ገዝተኀኛል ከእንግዲህ ምን ያሰጋኛል የዚች ምድር አይደለሁምና በስምህ ላብዛልህ ምሥጋና በደሌን ሽረሃል እኔን ግን ወደሃል ሞቴን ወስደህ ከእኔ ሞትክልኝ መድህኔ (2x) የዳነን ማንነት ከአንተ አግኝቻለሁ ሥጋቴን ጭንቀቴን ለአንተው ትቼዋለሁ ፍፁም ሰላም በአንተ ከአንተ ሆኖልኛል ለዘለዓለም መኖር መብቱ ተሰጥቶኛል አዝ:- በዋጋ ገዝተኀኛል ከእንግዲህ ምን ያሰጋኛል የዚች ምድር አይደለሁምና በስምህ ላብዛልህ ምሥጋና በደሌን ሽረሃል እኔን ግን ወደሃል ሞቴን ወስደህ ከእኔ ሞትክልኝ መድህኔ (2x) የፈሰሰልኝ ደም በእውነት ደምህ ነው ሕይወት የሆነልኝ ሙት ለነበርኩት ሰው እንዳልጠፋ አድርገህ አንተ አድነኀኛል ላደረክልኝ ሁሉ መልሴ ያንስብሃል አዝ:- በዋጋ ገዝተኀኛል ከእንግዲህ ምን ያሰጋኛል የዚች ምድር አይደለሁምና በስምህ ላብዛልህ ምሥጋና በደሌን ሽረሃል እኔን ግን ወደሃል ሞቴን ወስደህ ከእኔ ሞትክልኝ መድህኔ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection