በባዶነቴ አግኝተኀኛል አንተ እኔን መውደድ ያስገርመኛል አወዳደድህ ከመውደድ ያልፋል ወደድኩህ ብልህ ምን ያስገርማል ለምንድን ነው አልልህም ስራህ ጠፍቶኝ አልጠይቅህም የምልህ ግን አንድና ግልጽ ነው ስለወደድከኝ ወድጄሃለሁ አዝ:- እወድሃለሁ አሳብዬ እወድሃለሁ (2x) ስለወደድከኝ አሳብዬ ወድጄሃለሁ (2x) ወድጄሃለሁ ወድጄሃለሁ ለመውደዴ ገደብ የለኝም ምገልጸበት ቋንቋም አላገኝም ብቻ ነፍሴ አፍቅራሃለች እንደወደድካት ትወድሃለች አዝ:- እወድሃለሁ አሳብዬ እወድሃለሁ (2x) ስለወደድከኝ አሳብዬ ወድጄሃለሁ (2x) የአንተ ፍቅር መውደድህ አያልቅም መውደዴ ግን የአንተን ፍፁም አይገልጸውም አይገልጸውም ብዬ እንዴት ዝም እላለሁ በትንሿ ልቤ አቅሜ ቢሆንም ይሄው እወድሃለሁ አዝ:- እወድሃለሁ አሳብዬ እወድሃለሁ (2x) ስለወደድከኝ አሳብዬ ወድጄሃለሁ (2x) እወድሃለሁ (3x)