Song Lyrics

አግዘኝ

Hana Tekle
Agizegn
ለውድቀት መሮጤ ምንድነው ማዳንህ የገባኝ ጥንት ነው አባቴ ልጄ አንቺ የኔ እያልክ የጎረቤት ኑሮዬ ናፈቀኝ ጥፋቱ ከጠላት ወይ ከኔ ገብቶኝ እንዳልገባው መሆኔ አመል ካልሆነብኝ በስተቀር አሁን ምን ይገኛል ጠላት ሰፈር አዝ:- አግዘኝ ደግፈኝ ብቻዬን አቅም የለኝ ያየህልኝን ቁም ነገር እንዳላጣው በተራ ነገር (2x) ማን አየኝ አላየኝ ኑሮዬን አልደብቀው ካንተ ገበናዬን ሰው ፈርቶ ሰው ሸሽቶስ እስከመቼ ልኑር መጀመሪያ አንተን ፈርቼ እንዳልሞት ነበረ መዳኔ ፈቅደህ የሞትክልኝ ካህኔ እያወኩ ከገባሁ ከእሳቱ ማን ሊመልሰኝ ነው ማን ብርቱ አዝ:- አግዘኝ ደግፈኝ ብቻዬን አቅም የለኝ ያየህልኝን ቁም ነገር እንዳላጣው በተራ ነገር (2x) ነጻነቴም በዛ መሰለኝ ምን አለበት ኑሮ ለመደኝ ቀለለኝ የጥፋት መንገዴ ላይቀርልኝ ካለፈ መንደዴ የማውቀውን እውነት ሳልገፋ ከበር መልስ ሳልሆን ሳልጠፋ ብላቴናነቴን ታደገው አውለው ከቤትህ ከሚበጀው አዝ:- አግዘኝ ደግፈኝ (ደግፈኝ) ብቻዬን አቅም የለኝ (ብቻዬን አቅም የለኝ) ያየህልኝን ቁም ነገር (ያየህልኝን ቁም ነገር) እንዳላጣው በተራ ነገር (እንዳላጣው ተራ ነገር) (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection